የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የጅግጅጋ ከተማ ኮሪደር ልማት የምስራቋን ኮከብ ወርቃማ የውበት ድባብ አልብሷታል - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

Jul 31, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 23/2017(ኢዜአ)፦ የጅግጅጋ ከተማ ኮሪደር ልማት የምስራቋን ኮከብ ወርቃማ የውበት ድባብ አልብሷታል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰተላለፉት መልዕክት ዛሬ በከተማዋ በምሽት ተዘዋውረን ባደረግነው ምልከታ ከስምንት ወራት በፊት በሁለት ምዕራፍ የተጀመሩ ስራዎች በማጠናቀቂያ ምዕራፍ ላይ መሆናቸውን አይተናል ብለዋል።

የኮሪደር ልማቱ የከተማዋን የአስፋልት መንገዶች ያሰፋ፣ የእግረኛና የብስክሌት መንገዶችንም ያካተተ ነው። የህዝብ መዝናኛ ቦታዎችን ትኩረት ተሰጥቷቸዋል ሲሉም ገልጸዋል።


የወጣቶችና ታዳጊዎች ስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች፣ የተሽከርካሪ ማቆሚያ፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ ኃይል መሙያ ጣቢያዎችም በመገንባት ላይ ናቸው ነው ብለዋል፡፡

ከተማዋ ለክልሉ ከተሞች ሞዴል በሚሆን መልኩ ሰፊ የልማት ጎዳና ላይ ስትሆን የከተማዋ የቆየ ችግር የነበረውን ጎርፍ ለመከላከል የሚያስችሉ ማፋሰሻዎች፤ የተቀናጀ የውሃ፣ የመብራት፣ የቴሌኮምና የመንገድ መሠረተ ልማት ዝርጋታዎችም ይበሉ የሚያሰኙ ናቸው ሲሉም አክለዋል፡፡


በአጠቃላይ በከተማዋ እየተሰሩ ያሉ የልማት ስራዎች ባለሀብቶች በከተማዋ በሆቴል አገልግሎት እና ሌሎች ዘርፎች ተሰማርተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ ምቹ ሁኔታን እየፈጠሩ ይገኛሉ ሲሉ ነው የገለጹት በመልዕክታቸው፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.