ይርጋለም ፤ ሐምሌ 15/ 2017 (ኢዜአ)፦በይርጋለም ከተማ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት አዝጋሚ የነበረውንየከተማዋን የልማት ሂደት በፍጥነት እየቀየረ መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎች ተናገሩ።
የለውጡ መንግስት ከተሞች ለኑሮና ለኢንቨስትመንት ተመራጭ እንዲሆኑ የተገበራቸው የአስፓልት መንገድ፣ የኮሪደርና የአረንጓዴ ልማት ስራዎች የነዋሪውን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት ማሳደጋቸውን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፡፡
ከከተማዋ ነዋሪዎች መካከል አቶ መርጢቻ ማሞ እንደተናገሩት በይርጋለም ከተማ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት የከተማዋን አዝጋሚ የእድገት ሂደት በፍጥነት እየቀየረ በመሆኑ ህዝቡ ከመንግስት ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ ነው፡፡
የኮሪደር ልማቱ ከዚህ ቀደም ቆሻሻ ይጣልባቸው የነበሩ ቦታዎችን በማልማት ወደ መዝናኛነት ከመቀየሩም ባለፈ ለወጣቶች የስራ እድል መፍጠሩን ተናግረዋል፡፡
በከተማዋ እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማት እድገቷን በማፋጠን የነዋሪውን ተጠቃሚነት የሚያሳድግ በመሆኑ ለልማቱ ይዞታቸውን በፈቃደኝነት ማንሳታቸውን የገለጹት ደግሞ ሌላኛዋ አስተያየት ሰጪ ወይዘሮ አዳነች እሸቴ ናቸው፡፡
የአስፓልት መንገዱ ግንባታና ሌሎች መሰረተ ልማቶች እንዲፋጠኑ ድጋፋቸውን እንደሚያጠናክሩም ተናግረዋል፡፡
የመሰረተ ልማት ስራዎች መጠናቀቅም ከተማዋን ለኢንቨስትመንትና ለኑሮ ተመራጭ ከማድረጉም ባለፈ ለንግድ ስራቸው ተጨማሪ አቅም እንደሚሆን የተናገሩት ደግም አቶ ፍስሃ ግድየለው ናቸው።
ስራውንም ለማፋጠን በሚደረገው ሂደት ለአስፓልት መንገዱና ኮሪደር ልማት ስራው ይዞታቸውን ማንሳታቸውን ተናግረዋል፡፡
የይርጋለም ከተማ ከንቲባ አቶ ተረፈ ሙሉነህ በበኩላቸው በከተማዋ በተከናወነው የመጀመሪያው ምእራፍ የኮሪደር ልማት ስራ ከ1 ነጥብ 2 ሄክታር በላይ አረንጓዴ ልማትና የመዝናኛ ስፍራ መካተቱን ተናግረዋል፡፡
ተግባሩን በማስቀጠልም አረንጓዴ ልማት፣ ዘመናዊ መጸዳጃ ቤቶች፣ መዝናኛ ስፍራዎች፣ የእግረኛና የብስክሌት መንገዶችን ያካተተ ሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት ስራ እየተከናወነ ነው ብለዋል፡፡
ከተማዋን ለኑሮ ምቹ በማድረግ በጎብኚዎች ተመራጭ እንድትሆን ህዝቡን በማሳተፍ የልማት ስራዎቹ እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በዚህም ህዝቡ ይዞታውን በፈቃደኝነት በማንሳት ለልማት ስራው ጉልህ አበርክቶ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው የተጀመሩ ስራዎች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ በትኩረት ይሰራል ብለዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025