አዲስ አበባ፤ሐምሌ14/2017(ኢዜአ)፡-የ2018 በጀት አመት ከተጠናቀቀው በጀት አመት የበለጠ ስኬት ለማስመዝገብ በትኩረት የምንሰራበት ነው ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2017 በጀት አመት ውጤታማ ለሆኑ ተቋማት ዕውቅና እና ሽልማት አበርክቷል።
በዚህም ከፍተኛ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ተቋማት፣ ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች የመኪና እና የምስክር ወረቀት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በወቅቱ እንደገለጹት፥ ከተማ አስተዳደሩ በ2017 በጀት አመት ከፍተኛ አፈጻጸም በማስመዝገብ ውጤታማ ሆኗል።
ውጤቱ የተገኘው ጠንክሮ በመስራት መሆኑን የጠቆሙት ከንቲባዋ፤ ስኬት ያስመዘገቡትን እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ለበለጠ ስራ እንዲተጉ አሳስበዋል።
ተቋማቱ የከተማዋ ልማት እንዲፋጠንና የነዋሪዎቿ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ጠንክረው መስራታቸውን አስታውቀዋል።
የዕውቅና መርኃ ግብሩ ከፍተኛ ውጤት ያመጡትን ይበልጥ የሚያበረታታ ሌሎችንም በቁጭት የሚያነሳሳ መሆኑን አንስተዋል።
የ2018 በጀት አመት የበለጠ ውጤታማ ለመሆን የምንሰራበት ነው ያሉት ከንቲባዋ፥ ዕውቅናው ለቀጣይ ስራ ስንቅ እንደሚሆን ነው ያስታወቁት።
ሽልማት እና ዕውቅና የተሰጣቸው ተቋማት፣ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች በበኩላቸው፥ የተሰጣቸው እውቅናና ሽልማት በቀጣይ ጠንክረው በመስራት የበለጠ ውጤታማ ለመሆን እንደሚያነሳሳቸው ገልጸዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025