አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 13/2017(ኢዜአ)፦ በመዲናዋ በየዘርፉ ለተመዘገቡ ስኬቶች ከህዝቡ ጋር ተቀራርቦ መስራቱ ጉልህ ሚና መጫወቱን የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ከተማ አስተዳደሩ የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ውይይት ዛሬም ቀጥሎ ተካሂዷል።
በውይይቱ የተከናወኑ ተግባራት፣ የተገኙ ስኬቶች፣ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ ከውይይቱ ተሳታፊዎች ጥያቄዎች ተነስተው በመዲናዋ ከፍተኛ አመራሮች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት እንዳሉት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የነዋሪውን ተጠቃሚነት ከፍ ያደረጉ ስራዎች ተከናውነዋል።
በተለይም ህብረተሰብን በማሳተፍ በርካታ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ወደ አገልግሎት ማስገባት መቻሉን ጠቅሰው፤ ውጤቱ ከተማ አስተዳደሩ ህዝብን በማሳተፍ ስኬታማ ስራ እያከናወነ ስለመሆኑ ማሳያ ነው ብለዋል።
በበጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ በአቅመ ደካሞች ቤት ዕድሳት፣ በማዕድ ማጋራት የተገኙ ስኬቶች ተጠቃሽ መሆናቸውንም አብራርተዋል።
የሰው ተኮር ተግባራትን ማጠናከር ከዋና ዋና ተልዕኮዎች አንዱ መሆኑን የገለጹት ከንቲባዋ፤ በዚህ ረገድ ይበልጥ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ መትጋት አለብን ብለዋል።
የኑሮ ውድነትን መቀነስና በመሰረተ ልማት አቅርቦት ላይ አበረታች ውጤቶች መኖራቸውን ጠቅሰዋል።
ከማህበረሰቡ የልማት ፍላጎት አኳያ አሁንም ብዙ መስራት ይጠበቅብናል ያሉት ከንቲባ አዳነች የስራ ባህልን ማሻሻል፣ የተቋም ግንባታ ማጠናከር፣ አገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል ከቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች መካከል እንደሚገኙበት ገልፀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃላፊ ጃንጥራር አባይ በበኩላቸው የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር የምርት አቅርቦት እንዲጨምር እየተሰራ ያለው ስራ መቀጠሉን ተናግረዋል።
ሸማቹ የፍጆታ ምርቶችን በቀጥታ ከአምራቹ የሚያገኝባቸው ማዕከላት ተገንብተው ወደ ስራ መግባታቸውንም ገልጸዋል።
በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ሞገስ ባልቻ፤ በአመራሩ ረገድ የድጋፍ እና
ክትትል ባህል መዳበሩ ለተገኘው ውጤት አስተዋጽኦ ማበርከቱን ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025