አዲስ አበባ፤ሐምሌ 12/2017 (ኢዜአ):-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተጠናቀቀው የ2017 በጀት አመት የህብረተሰቡን የልማት ፍላጎት ያሳኩ ስራዎች መከናወናቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ውይይት ማካሄድ ጀምሯል።
በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈጉባኤ ቡዜና አልከድር፣በብልፅግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርጫፍ ጽህፈት ቤት ሀላፊ ሞገስ ባልቻ እንዲሁም የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎቾ ተገኝተዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅት እንዳሉት የ2017 በጀት አመት ስኬታማ አመት መሆኑን ገልጸው፥አጠቃላይ የእቅድ አፈጻጸሙ 95 በመቶ ነው ብለዋል።
በበጀት አመቱ የህብረተሰቡን የልማት ፍላጎት ያሳኩ ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውንም ተናግረዋል።
የተከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶች ትርጉማቸው ከፍ ያለ መሆኑን አንስተው፤ በርካታ ህዝብ በጋራ የሚገለገልባቸው ስራዎች መሆናቸውንም ገልጸዋል።
የኑሮ ውድነትን ለመቆጣጠር በልዩ ትኩረት በርካታ ምርቶችን ወደ ከተማው እንዲገቡ በማድረግ ገበያን የማረጋጋት ስራ መከናወኑን ተናግረዋል።
ከስራ እድል ፈጠራ አንጻር ከእቅድ በላይ መከናወኑን የገለጹት ከንቲባዋ፤ ከገቢ አሰባሰብ አኳያም ጠንካራ ስራ መሰራቱን ነው የጠቀሱት።
በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በተከናወኑ ተግባራት በከተማዋ ባሉ ኢንዱስትሪዎች ላይ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን አንስተው፤ በዚህም ምርትና ምርታማነታቸው ማደግ ችሏል ብለዋል።
በኮሪደር ልማት የከተማዋን ጽዳት፣ውበት እንዲሁም ገጽታ በከፍተኛ ሁኔታ መቀየር መቻሉን ገልጸዋል።
ይህም ከተማዋን ለኑሮ ምቹና ቱሪዝምን በከፍተኛ መጠን የምትስብ ማድረግ ተችሏል ነው ያሉት።
ከብልጽግና መዳረሻ እና ከህዝቡ የልማት ፍላጎት አንጻር የተከናወኑ ስራዎች በቂ አለመሆናቸውን ያነሱት ከንቲባዋ፤ በ2018 በጀት አመት ከስኬቶች ትምህርት በመውሰድ ዘላቂ ለማድረግ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025