ደብረማርቆስ፤ ሐምሌ 11 /2017(ኢዜአ)፡ - በምሥራቅ ጎጃም ዞን አርሶ አደሮች አሲዳማ አፈርን በኖራ አክመው የእርሻ ማሳቸውን በማልማት ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ መቻላቸው ተገለጸ።
ዘንድሮ ምርታማነትን በማሳደግ በምግብ ራስን ለመቻል ትኩረት ከተሰጠው ጉዳይ አሲዳማ አፈርን በማከም ማልማት እንደሆነ የዞኑ ግብርና መምሪያ አመልክቷል።
ከ248 ሄክታር በላይ መሬት በኖራ ለማከም ታቅዶ እስካሁን ከ48ሺህ ኩንታል በላይ ኖራ በማቅረብ በአርሶ አደሩ ማሳ ላይ መበተኑን መምሪያው ጠቅሷል።
አርሶ አደር መልሳቸው ያዜ በዞኑ የማቻከል ወረዳ የቅዳማን ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ፤ በአሲዳማ አፈር የተጠቃ አንድ ሄክታር የእርሻ ማሳቸውን በኖራ በማከም ምርታማነታቸውን ማሳደግ እንደቻሉ ለኢዜአ ተናግረዋል።
ይህም የመሬታቸውን ለምነት በመጨመሩ በሄክታር ከአምስት ኩንታል በላይ የምርት ጭማሪ ማግኘታቸውን ጠቅሰዋል።
በተያዘው የመኸር ወቅትም ተግባሩን ለማስቀጠል ጠንክረው እየሰሩ መሆኑን አስረድተዋል።
በአነደድ ወረዳ የጉዳለማ ቀበሌ አርሶ አደር ተመስጌን ክብረት በበኩላቸው፤ ግማሽ ሄክታር ማሳቸውን በኖራ በማከም የአፈሩ ለምነት እንዲመለስ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
ቀደም ሲል በአሲድ የተጠቃው ማሳቸው ምርቱ መቀነሱን አውስተው፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተጠቃው ማሳቸው በኖራ አክመው በመዝራት የጤፍና የስንዴ ምርታቸው ላይ ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱን ተናግረዋል።ያገኙትን ጥቅም ለማሳደግም ከዘር በፊት ቀደም ብለው ኖራ በመበተን ማከማቸውን አንስተዋል።
የምሥራቅ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ ሃላፊ አቶ አበበ መኮንን እንደገለጹት፤ ዘንድሮ ምርታማነትን በማሳደግ በምግብ ራስን ለመቻል ትኩረት ከተሰጠው ጉዳይ አሲዳማ አፈርን በማከም ማልማት ነው።
ለዚህም በዞኑ ከ248 ሄክታር በላይ መሬት በኖራ ለማከም ታቅዶ እስካሁን ከ48ሺህ ኩንታል በላይ ኖራ በማቅረብ በአርሶ አደሩ ማሳ ላይ መበተኑን ተናግረዋል።
አርሶ አደሮችን በማሳተፍ እየተካሄደ ያለው አሲዳማ አፈርን በኖራ የማከም ተግባር ውጤታማነቱ በየጊዜው እየጨመረ መምጣቱን አስረድተዋል።
ከግብርና መምሪያው የተገኘው መረጃ እንደሚያመልክተው፤ በምሥራቅ ጎጃም ዞን በ2017/2018 የምርት ዘመን ከ642 ሺህ ሄክታር በላይ በሰብል ዘር በመሸፈን ከ25 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ ወደ ተግባር ተገብቷል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025