አዲስ አበባ፤ሐምሌ 12/2017 (ኢዜአ):-የሳንቲም ፔይ የፖስ መገጣጠሚያ ፋብሪካ እና የክፍያ ስዊች ስርዓት በአገራችን የዲጂታል ክፍያ ስነምህዳር አንድ ተጨማሪ አቅም ይሆናል ሲሉ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
የሳንቲም ፔይ የፖስ መገጣጠሚያ ፋብሪካ እና የክፍያ ስዊች ሥርዓት ምርቃት ተከናውኗል፡፡
በመርሃ ግብሩ ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስትና የግል የፋይናንስ ዘርፍ የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ፋብሪካው ለኢትዮጵያ የዲጂታል ሥነ ምህዳር እድገት ተጨማሪ አቅም ይፈጥራል፡፡
ባለፉት አመታት ከጥሬ ገንዘብ ዝውውር በበለጠ የዲጂታል ሥርዓት ክፍያ አፈጻጸም ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ትግበራ የጎላ አበርክቶ እንደነበረው አንስተዋል፡፡
በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ለተገኙ ድሎች የግሉ ዘርፍ ተሳትፎ የጎላ እንደነበር አስታውሰው፥ ስኬቱን በዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ለመድገም የበለጠ ትብብርና ትጋት ይጠይቃል ብለዋል፡፡
የሳንቲም ፔይ የፖስ መገጣጠሚያ ፋብሪካ የውጭ ምንዛሪ ወጪን ከማስቀረት ባለፈ ለቴክኖሎጂ ሽግግርና ተደራሽነት የጎላ አበርክቶ እንዳለው ገልጸዋል፡፡
የሀገር ውስጥ ምርትን ማበረታታት ከዋጋ እና ከአቅርቦት በላይ የሀገር ደህንነትን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑንም አንስተዋል፡፡
ለኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ዘርፍ ማንሰራራት ሚናው የጎላ መሆኑን ገልጸው፤ ማሽኖችን ከትናንሽ ሱቆች እስከ ታላላቅ ድርጅቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ እንደሚያስችልም እንዲሁ፡፡
ሳንቲም ፔይ የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ማንሰራራት አንዱ ማሳያ መሆኑን በመጥቀስ፤ የኢትዮጵያ ስታርታፕ አዋጅ የቴክኖሎጂ ፈጠራን በማበረታታት ኢትዮጵያውያንን የቴክኖሎጂ ባለቤት የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የ "OpenWay" ስዊች ሥርዓት ዓለም የደረሰበትን ፈጣንና ደህንነቱ የተረጋገጠ ክሬዲት ካርድ፤ ቨርቹዋል ካርድ እና ዘመናዊ የክፍያ ሥርዓት ገቢራዊ ማድረግ ያስችላል ብለዋል፡፡
የሳንቲም ፔይ ፋይናንስ ሶሉሽን አክስዮን ማህበር ስራ አስፈጻሚ ትንሳኤ ደሳለኝ በበኩላቸው፥ ፋብሪካው ለኢትዮጵያ የዲጂታል ፋይናንስ ስርዓት አጋዥ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ፖስ ማሽኖቹ በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የሚገጣጠሙና በራሳቸው የበለጸጉ መተግበሪያዎችን የያዙ ለባንኮችና ለንግድ ተቋማት የሚያገለግሉ መሆኑንና ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር በቀን እስከ ሶስት ሺህ ዘመናዊ ፖስ ማሽኖችን ያመርታል ብለዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025