ሐረር ፤ ሐምሌ 9/2017 (ኢዜአ)፦ በሐረር ከተማ በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር በዶሮ እርባታና እንቁላል ምርት በመሰማራት ተስፋ ሰጪ ስራ እየተከናወነ መሆኑን በከተማው በዘርፉ የተሰማሩ ወጣቶች ተናገሩ፡፡
በክልሉ አምራችነትን የሚያጎለብት የስራ እድል ፈጠራ ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑን የገለጸው ደግሞ የክልሉ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ቢሮ ነው።
ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በምህንድስና ተመርቆ በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር በዶሮ እርባታ የተሰማራው ኢንጂነር አንዋር ሸምሰዲን "ስራ ፈጥሬ መንቀሳቀሴ ከራሴ ባለፈ ለሌሎች ዜጎች የስራ እድል እንዳመቻች አስችሎኛል" ብሏል።
"በአሁኑ ወቅት ስራዬን ከሐረር ባለፈ ወደ ምስራቅ ሐረርጌ ዞን ወረዳዎች ለማዳረስ እየሰራሁ እገኛለሁ" ያለው ኢንጅነር አንዋር፤ በተለይም በአሁኑ ወቅት ከዶሮ እርባታውና እንቁላል ባለፈ ፍጉን ለማዳበርያነት እንዲያገለግል እየሰራ ስለመሆኑ ተናግሯል።
በግል ተነሳሽነት የተሻሻሉ የዶሮ ዝርያን በመውሰድ የዶሮ እርባታ ስራ መጀመሩን የሚገልጸው ወጣት ኤልያስ ጌታቸው ደግሞ በአሁን ጊዜ መንግስት ባደረገላቸው የብድርና የስራ ቦታ የተሻለ ስራ እያከናወነ መሆኑን ተናግሯል።
በአጭር ጊዜ በጀመረው የዶሮ እርባታ ስራ መሻሻሎችን እያሳየ እንደሚገኝ የጠቆመው ወጣት ኤልያስ ዶሮንና እንቁላልን ለአጎራባች ክልሎች ለማሰራጨት እቅድ ይዞ እየሰራ መሆኑን ተናግሯል።
ከአራት ሺህ በላይ ዶሮዎች ማድረሱን የሚናገረው ብርሃኑ አበራም ከዚህ ጎን ለጎን የዶሮ መኖን ከሌላ አካባቢ በማምጣት በተመጣጣኝ ዋጋ በማከፋፈል እራሱንና ቤተሰቡን እየጠቀመ መሆኑን ገልጿል።
ዘርፉ እራስን ከመጥቀም ባለፈ የገበያ ዋጋ ንረትን ለማረጋጋት የጎላ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጾ፤ በመሆኑም ከዚህ የተሻለ ስራ ለማከናወን ማቀዱን ተናግሯል።
የክልሉ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ አቶ ኡስማኢል ዩስፍ እንዳሉት በክልሉ አምራችነትን በሚያጎለብት የስራ እድል ፈጠራ ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ ነው።
በዚህም ለዜጎች የስራ እድልን ከመፍጠር ባለፈ ምርትን ወደ ገበያ በማቅረብ ህብረተሰቡ የፍጆታ እቃዎችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ እያስቻለና ውጤት እያስገኘ መሆኑን ተናግረዋል
በተለይም በ2017 በጀት ዓመት ስምንት ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፈጠሩን የጠቆሙት አቶ ኡስማኢል፤ ከዚህ ውስጥ 43 በመቶ ሴቶች መሆናቸውን ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025