ሐረር፤ ሐምሌ 3/2017(ኢዜአ)፦ በሐረሪ ክልል በ2017 በጀት ዓመት 24 አዳዲስ አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ መግባታቸውን የክልሉ ኢንተርፕራይዝ ልማትና ኢንዱስትሪ ቢሮ አስታወቀ።
በክልሉ ወደ ስራ የገቡ ኢንዱስትሪዎች ለዜጎች የስራ እድል እየፈጠሩ መሆኑም ተገልጿል።
የክልሉ ኢንተርፕራይዝ ልማትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ ኡስማኢል ዩስፍ ለኢዜአ እንደገለጹት በክልሉ በተለይም የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የአምራች ኢንዱስትሪውን የማምረት አቅም ከማጎልበት ባለፈ በዘርፉ መነቃቃት እንዲፈጥር እያስቻለ ነው።
በክልሉ ወደ ስራ የገቡት ኢንዳስትሪዎች ወደ ውጪ የሚላኩ ምርቶችን በማጎልበትና ተኪ ምርቶችን በማምረት የውጪ ምንዛሬን እያስቀሩና ከፍተኛ ሚና እያበረከቱ እንደሚገኙም ገልጸዋል።
በክልሉም በ2017 በጀት ዓመት ሰባት መካከለኛና 17 አነስተኛ አዳዲስ ኢንዳስትሪዎች ወደ ስራ መግባታቸውንና እነዚህም 383 ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የስራ እድል መፍጠራቸውን አክለዋል።
በተለይም ዘንድሮ በክልሉ ለአምራች እንዱስትሪዎች 579 ቶን የሚሆን ግብዓት መቅረቡን ጠቁመው ለአምራች እንዱስትሪዎቹ ከመሰረተ ልማት ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮችን የመቅረፍ ስራ መከናወኑንም አመላክተዋል።
መንግስት የጀመረውን የአረንጓዴ ልማት ለማጎልበት ፋብሪካ ከፍተው የፕላስቲክ ፌስታል በከረጢት የመተካት ስራ መጀመራቸውን የተናገሩት ደግሞ የታቴ የከረጢት ፋብሪካ ባለቤት አቶ አቡበከር አዲል ናቸው።
ፋብሪካው በቀን ከ150ሺህ እስከ 200ሺህ ከረጢት እንደሚያመርት ጠቁመው በተለይም ለዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል እንደፈጠሩም ተናግረዋል።
በከተማው የሚገኘው የረሃ ፎም ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ ኡመር ሳሊህ በበኩላቸው በአልባሳት በኩል ተኪ ምርቶችን በማምረት ለአካባቢው ህብረተሰብና ተቋማት ለገበያ እያቀረቡ መሆኑ በመጥቀስ በቀጣይም ምርታቸውን በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል ለማዳረስ እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።
በፋብሪካዎቹ የስራ እድል የተፈጠረላቸው ወጣቶች እንደሚናገሩት የስራ እድል ተፈጥሮላቸው እራሳችውንና ቤተሰባቸውን ከመደጎም ባለፈ ልምድ እየቀሰሙና በትርፍ ጊዜያቸውም የኮሌጅ ትምህርት እንዲከታተሉ እድል እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል።
በሐረሪ ክልል 165 ከፍተኛ፣ መካከለኛና አነስተኛ አምራች ኢንዳስትሪዎች በማምረት ስራ ላይ ናቸው።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025