ሸካ፤ ሰኔ 30/2017(ኢዜአ)፦ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል የመስኖ አውታሮችን በማስፋፋት የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት መሰጠቱን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር ኢ/ር) ገለጹ።
ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ በሸካ ዞን በየኪ ወረዳ ከ37 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባ አነስተኛ የመስኖ ፕሮጀክት መርቀዋል።
በወረዳው አላሞ ቀበሌ የተገነባው ቡቢ አነስተኛ የመስኖ አውታር ከ66 ሄክታር በላይ መሬት በማልማት ከ800 በላይ ቤተሰቦችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑ ታውቋል።
የክልሉ መንግስት የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የመስኖ አውታሮችን ማስፋፋት ላይ አተኩሮ እየሰራ ነው ብለዋል።
ይህም ክልሉ ያለውን የግብርና አቅም አሟጦ ለመጠቀምና የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ጉልህ ሚና እንዳለው ጠቅሰዋል።
ባለፉት አራት ዓመታት 22 የመስኖ ፕሮጀክቶች ተገንብተው የእርሻ ሥራን ለማዘመን እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው በዚህም ከ1 ሺህ 400 ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ማልማት እንደተቻለ ተናግረዋል።
በቀጣይም የተለያዩ አካባቢዎች ላይ የመስኖ ፕሮጀክቶች ግንባታን በማጠናከር የክልሉን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይሠራል ብለዋል።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የክልሉና የዞን እንዲሁም የወረዳ አመራሮችና የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025