
አዳማ ፤ሰኔ 23/2017 (ኢዜአ)፡-የእንስሳት ጤና ኤክስቴንሽንን ውጤታማ በማድረግ የእንስሳት ዘርፍ ልማቱን ለማዘመን ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር ገለፀ።
የእንስሳት ጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጅ መመሪያና ፕሮግራም ለክልሎችና ባለድርሻ አካላት የማስተዋወቅ መድረክ በአዳማ ተካሄዷል።

የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር) በተለይ ለኢዜአ እንደገለፁት የእንስሳት ሀብት ልማቱን ለማዘመን ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ ይገኛሉ።
በተለይ በሌማት ትሩፋት ፕሮግራም የወተት ላሞች ዝሪያን ከማሻሻል ጀምሮ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።
በዚህም በወተት ላሞች ማዳቀል፤ የተሻለ ምርት በሚሰጡ በዘመናዊ የዶሮና ዓሣ እርባታ፤ እንዲሁም በንብ ልማት ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

ይሁን እንጂ ከጤና አንፃር የእንስሳት ሀብት ጥራት፣ ደህንነትና ምርታማነትን ለማረጋገጥ የእንስሳት ኤክስቴንሽን ስትራቴጂ ተቀርጾ ወደ ተግባር መገባቱን ገልጸዋል።
ለዚህም የእንስሳት ጤና ፓኬጅ፣ መመሪያና ፕሮግራም መዘጋጀቱን ሚኒስትር ዴኤታው ገልፀው ለተፈፃሚነቱ በቅንጅት ለመረባረብ መድረኩ መሰናዳቱን ጠቁመዋል።
የእንስሳት ጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጅ የዘርፉን ልማት ከማዘመንና ምርታማነቱን ከማሳደግ አኳያ ወሳኝ ሚና እንዳለውም ተናግረዋል።

ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል የኦሮሚያ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ቶሌራ ደበላ በበኩላቸው የእንስሳት ጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጁ የዘርፉን ልማት ለማዘመን የጎላ ፋይዳ አለው ብለዋል።
በክልሉ የወተት ላሞች፣ የዶሮ፣ የዓሣ፣ የንብና የስጋ እንሳሳት ኢንሼቲቮች ተቀርፆ ተግባራዊ እየተደረጉ ናቸው ያሉት አቶ ቶሌራ በዚህም በክልሉ የእንስሳት ሀብት ልማትና ዕድገት ላይ ተጨባጭ ውጤት እየመጣ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
የእንስሳት ጤና ኤክስቴንሽን ፓኬጅና ፕሮግራምን ከክልል እስከ ወረዳና ቀበሌ ድረስ በማውረድ ለመተግበርና ውጤታማነቱን እውን ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰራም ምክትል ቢሮ ኃላፊው አረጋግጠዋል።
አዲስ አበባ፤መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ከሀገራዊ ጥቅም ባለፈ ለዓለም አቀፍ የንግድ መስመር ደህንነትን ...
Apr 8, 2026
ዲላ ፤ መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦የለውጥ ዓመታቱን ጉዞ ስንዘክር ያስመዘገብናቸውን ስኬቶች በማስቀጠል መሆን አለበት ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ር...
Apr 8, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ንግድና ኢንቨስትመንት ስኬት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ተግባራዊ ውጤት ማሳያ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ...
Mar 27, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የብዝኅ ኢኮኖሚ ልማት የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ አህጉራዊ የኢንቨስትመንት ማዕከልነትን እያረጋገጠ ...
Mar 26, 2026