ጎንደር፤ ሰኔ 17/2017(ኢዜአ)፡- መንግስት ሰላሙን ከማፅናቱ ጎን ለጎን ልማትን በፍጥነት ማስፈፀም እንደሚቻል በመላ ሀገሪቱ በውጤታማነት የቀጠሉት የኮሪደር ልማትና ከተሞችን የማስዋብ ፕሮጀክቶች አመላካቾች ናቸው ሲሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ ተናገሩ፡፡
ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ የሚዲያና የኮሙኒኬሽን አመራሮችና ባለሙያዎች በጎንደር ከተማ በፌደራልና በክልሉ መንግስት እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል፡፡
በዚህ ወቅት የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ፤ መንግስት ሰላሙን ከማፅናቱ ጎን ለጎን ልማትን በፍጥነት ማስፈጸም እንደሚቻል በመላ ሀገሪቱ እየተካሄዱ የሚገኙ የኮሪደር ልማትና ከተማ የማስዋብ ፕሮጀክቶች አመላካቾች እንደሆኑ ገልጸዋል።
ጎንደር የቀደመ ስሟንና ዝናዋን የሚመጥን የልማት ተቋዳሽ ሳትሆን ለዘመናት መቆየቷን አስታውሰው፤ አሁን ላይ የኮሪደር ልማትን ጨምሮ በከተማዋና አካባቢዋ እየተገነቡ የሚገኙ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ወደ ቀደመ ክብሩዋ የሚመልሱ ናቸው ብለዋል፡፡
የከተማዋን የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር በዘላቂነት ይፈታል ተብሎ ላለፉት 17 ዓመታት ግንባታው ሲጓተት ቆይቶ ኋላም ቆሞ የነበረው የመገጭ የመስኖና የመጠጥ ውሃ ግድብ ፕሮጀክት ዳግም ግንባታው መጀመር የመንግስትን የማስፈጸም አቅም፣ ብቃትና ቁርጠኝነት ያመላከተ መሆኑን አንስተዋል፡፡
የሀገራችን የብዝሃ ታሪክና የስልጣኔ መገለጫ የሆነው የአጼ ፋሲል ቤተ መንግስት እድሳትና ጥገና ስራም መንግስት ታሪክን ጠብቆና ተንከባክቦ ለትውልድ ለማሻገር ያለውን ቁርጠኛ አቋም ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
''ሕዝቡ ልማቱን በመደገፍ እያሳየው ያለው ትብብርና ተሳትፎ ጎንደር ላይ በተከናወነው የኮሪደር ልማት ስራዎች ማረጋገጥ ችለናል'' ሲሉ ሚኒስትር ዴኤታው አስታውቀዋል።
ጎንደር ሰላሟንም ልማቷንም በአጭር ጊዜ ያረጋገጠች ከተማ መሆኑዋን አውስተው፤ ሀገራችንን ወደ ብልጽግና ጎዳና በአጭር ጊዜ ውስጥ ሊያስገቡ የሚችሉ የልማት ስራዎች በከተሞቻችን እየታየ ነው ብለዋል፡፡
የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎችና አመራሮች በሀገሪቱ እየተመዘገቡ ያሉ የለውጥና የልማት ስራዎችን ተከታትሎ በመዘገብ ለሌሎች ተሞክሮ እንዲሆን በትጋት መስራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
''የጎንደር ከተማ ሕዝብ የኮሪደር ልማቱን በመደገፍ የልማት አሻራውን አሳርፏል'' ያሉት የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ ደብሬ የኋላ ናቸው፡፡
ይህም ህንጻና መኖሪያ ቤቱን በማደስና በማስዋብ እንዲሁም ቀለም በመቀባትና መብራት በመዘርጋት ጭምር እንደሆነ ጠቅሰዋል።
የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎችና አመራሮቹ የመገጭ የመስኖና የመጠጥ ውሃ ግድብ ፕሮጀክትን ጨምሮ የከተማውን የኮሪደር ልማት እንዲሁም የአፄ ፋሲል አብያተ መንግስት የጥገናና የእድሳት ስራ እንቅስቃሴን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025