
ሀዋሳ፤ ሰኔ 4/2017(ኢዜአ)፦ በሲዳማ ክልል የአምራች ኢንዱስትሪውን አቅም በማሳደግ የክልሉን ህዝብ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉየክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ ገለጹ።
የክልሉ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ከሀዋሳ ዪኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በኢንዱስትሪ ልማት ላይ ባስጠናቸው ጥናቶች ዙሪያ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ተካሂዷል።
የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ እንደገለጹት የአምራች ኢንዱስትሪውን አቅም በማሳደግየክልሉን ህዝብ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ።

ዘርፉ የስራ ዕድል በመፍጠር፣ ተኪ ምርትን በማምረትና ቴክኖሎጂን በማሳደግ እንደክልል ለተጀመረው የቤተሰብ ብልጽግና የማረጋገጥ ግብ ሰፊ ድርሻ ያለው ብለዋል።
በዚህም የክልሉ መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ትኩረት ጥናትን መሰረት ያደረገ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመውበክልሉ ያለው ምቹ መሰረተ ልማት ኢንዱስትሪውን ለማስፋፋት እንደሚያግዝ ገልጸዋል።
በክልሉ ያለውን መሬትና የሰው ሃይል በመጠቀም ምርታማነትን በማሳደግ ለኢንዱስትሪ ግብዓት የሚሆኑ ምርቶች ላይ ማተኮርና ዘርፉን ማስፋፋት ልዩ ትኩረት የሚሰጠው አጀንዳ መሆኑንም ተናግረዋል።

የክልሉ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሀላፊ ጎሳዬ ጎዳና በበኩላቸው ቢሮው በክልሉ ያለውን የኢንዱስትሪ አቅም በተገቢው ለመጠቀም በጥናት የተደገፈ ስራ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ከሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የተዘጋጀው የኢንዱስትሪ ፍኖተ ካርታ ስትራቴጂክ እቅድ በክልሉ ያለውን የአምራች ኢንዱስትሪ አቅም በማሳደግ ዘርፈ ብዙ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል።
ዘርፉ የባለድርሻ አካላትን ቅንጅታዊ ስራ የሚጠይቅ በመሆኑ በምክክሩ የተገኙ ግብዓቶችን በማጠናከር ወደ ኢንዱስትሪ የሚደረገውንሽግግር ለማጠናከር በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል የክልሉ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ሃላፊ ዶክተር ኢንጂነር ከበደ ጋኖሌ ጥናቱ በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ያለውን አቅም ለይቶ መስራት የሚያስችል ነው።
እንደክልል በማዕድን ዘርፍ ያለው ትልቅ አቅም የኢንዱስትሪ ግብዓት የሚሆንና ሰፊ የስራ ዕድል የሚፈጥር በመሆኑ በጥናቱ ትኩረት ሊደረግበት ይገባል ብለዋል።
በጥናቱ የተለዩ የኢንዱስትሪ ክላስተሮች የአካባቢውን አቅም የለዩ መሆናቸው በተለየ ትኩረት እንድንሰራ የሚያስችልና ቅንጅት የሚጠይቅ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ሃላፊ መምሩ ሞኬ ናቸው።
በግብርናው ዘርፍም አትክልት ተኮር ኢንዱስትሪ ማስፋፋት የሚያስችል አቅም በክልሉ መኖሩን ተናግረዋል።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ትብብር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ታፈሰ ማቲዎስ በበኩላቸው የክልሉ መንግስት ልማትን ለማረጋገጥ ጥናትን መሰረት ያደረገ ስራ መጀመሩ ለሌሎች ክልሎች ተሞክሮ የሚሆን ነው ብለዋል።
በግብርናው ዘርፍ ያለውን አቅም በመጠቀምየግብርና ምርቶችን የሚያቀነባብሩ ኢንዱስትሪዎችን ለማሳደግ ከመድረኩ የተነሱ ግብዓቶችን በማካተት ጥናቱን ውጤታማ ለማድረግ በቅንጅት እንደሚሰሩ ገልጸዋል።
አዲስ አበባ፤መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ከሀገራዊ ጥቅም ባለፈ ለዓለም አቀፍ የንግድ መስመር ደህንነትን ...
Apr 8, 2026
ዲላ ፤ መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦የለውጥ ዓመታቱን ጉዞ ስንዘክር ያስመዘገብናቸውን ስኬቶች በማስቀጠል መሆን አለበት ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ር...
Apr 8, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ንግድና ኢንቨስትመንት ስኬት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ተግባራዊ ውጤት ማሳያ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ...
Mar 27, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የብዝኅ ኢኮኖሚ ልማት የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ አህጉራዊ የኢንቨስትመንት ማዕከልነትን እያረጋገጠ ...
Mar 26, 2026