
ጋምቤላ፤ ግንቦት 25/2017(ኢዜአ)፦ በጋምቤላ ክልል ለተጀመረው የልማትና የብልጽግና ጉዞ ስኬታማነት የንግዱ ማህበረሰብ ሁለንተናዊ ተሳትፎ ሊጠናከር እንደሚገባ ተመለከተ።
’’ለሁለንተናዊ ብልጽግና፣ የንግዱ ማህበረሰብ ሚና’’ በሚል መሪ ሃሳብ የንግዱ ማህበረሰብ የተሳተፈበት ውይይት ዛሬ በጋምቤላ ከተማ ተካሂዷል።
በብልጽግና ፓርቲ የጋምቤላ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አሽኔ አስቲን እንዳሉት መንግስት የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ ይገኛል።
በክልሉ ባለፉት የለውጥ ዓመታት የህዝቡን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተከናወኑ ስራዎች በርካታ ስኬቶች ተመዝግበዋል ብለዋል።
ይሁን እንጂ እየጨመረ የመጣውን የማህበረሰቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ፈላጎትና ጥያቄ ከመመለስ አኳያ ቀሪ ስራዎች መኖራቸውን አመልክተዋል።
መንግስት እየሰፋ የመጣውን የህዝቡን የልማት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ለሚያደርጋቸው ጥረቶች ስኬታማነት የንግዱ ማህበረሰብ ሁለንተናዊ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
የንግዱ ማህበረሰብ በተለይም በኢንቨስትመንት ዘርፍ በመሰማራት ኢኮኖሚውን በመደገፍ በኩል ያለውን ድርሻ ሊያጠናክር እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
የውይይት መድረኩ ዓላማ የንግዱ ማህበረሰብ እየተከናወኑ ባሉት የልማት ስራዎች ዙሪያ የጠራ ግንዛቤ በመያዝ የልማት አጋርነቱን እንዲያጠናከር ለማስቻል መሆኑን አስታውቀዋል።
የክልሉ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ምክልት ኃላፊ ኢንጂነር ኡሌሮ ኦፒዮው በበኩላቸው የንግዱ ማህበረሰብ የተረጋጋ የገበያ ስርዓት እንዲረጋገጥ ማድረግን ጨምሮ ለልማትና እድገት ሚናውን በበለጠ ሊወጣ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ከመድረኩ ተሳተፊዎች መካከል አቶ ዋንግ ኩላንግ በሰጡት አስተያየት መንግስት ህዝቡን የልማት ተጠቃሚ ለማድረግ እያደረገ ያለው ጥረት የሚበረታታ ነው ብለዋል።
በመንግስት የተጀመሩ የልማት ስራዎችን ለማገዝ ዝግጁ መሆናቸውንም ጨምረው አመልክተዋል።
የንግዱ ማህበረሰብ መንግስት ለጀመራቸው የልማት ስራዎች ሚናውን ይወጣል ያሉት ደግሞ ሌላው የመድረኩ ተሳታፊ አቶ ፍቃዱ ቀናው ናቸው።
አዲስ አበባ፤መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ከሀገራዊ ጥቅም ባለፈ ለዓለም አቀፍ የንግድ መስመር ደህንነትን ...
Apr 8, 2026
ዲላ ፤ መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦የለውጥ ዓመታቱን ጉዞ ስንዘክር ያስመዘገብናቸውን ስኬቶች በማስቀጠል መሆን አለበት ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ር...
Apr 8, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ንግድና ኢንቨስትመንት ስኬት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ተግባራዊ ውጤት ማሳያ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ...
Mar 27, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የብዝኅ ኢኮኖሚ ልማት የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ አህጉራዊ የኢንቨስትመንት ማዕከልነትን እያረጋገጠ ...
Mar 26, 2026