
ደብረ ብርሃን፤ግንቦት 16/2017(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በመታገዝ በተከናወኑ ተግባራት ባለፉት አስር ወራት 151 ኢንዱስትሪዎች ወደ ማምረት መሸጋገራቸውን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን(ዶ/ር) አስታወቁ።
በደብረብርሃን ከተማ በአንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር በላይ የተገነቡ ሶስት የአምራች ኢንዱስትሪዎች ዛሬ ተመርቀዋል።
በምረቃው መርሃ ግብር ላይ ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አብዱ ሁሴን(ዶር) እንደገለጹት፥ በክልሉ የሚከናወኑ የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ተግባራተ አበረታች ውጤት እያስመዘገቡ ነው።
ባለፉት አስር ወራት ብቻ "ኢትዮጵያ ታምርት እኛም እንሸምት" ንቅናቄ በመታገዝ 151 ኢንዱስትሪዎች ግንባታቸው ተጠናቆ ወደ ማምረት መሸጋገራቸውን አስታውቀዋል።
ወደ ማምረት የተሸጋገሩትም 56 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፍጠራቸውን ተናግረዋል።
የተጀመረውን የኢንዱስትሪ ልማት አጠናክሮ ለማስቀጠል የክልሉ ህዝብና ባለሀብቱ ለዘላቂ ሰላም መስፈን የጀመሩትን ጥረት አጠናክረው እንዲቀጥሉም አሳስበዋል።
በደብረ ብርሃን ከተማ ዛሬ የተመረቁት ኢንዱስትሪዎችም ከአርሶ አደሩ ጋር በማስተሳሰር በግብአት አቅርቦት ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ ናቸው ብለዋል።
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት በበኩላቸው፥በከተማዋ በኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚሳተፉ ባለሀብቶች ቁጥር እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል።
በዛሬው እለት ከአንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ በመገንባት ለምረቃ የበቁት ሶስት ፋብሪካዎችም ለዚህ ማሳያ ናቸው ብለዋል።
በቀጣይ የተጀመረውን ኢንዱስትራያላይዜሽን የበለጠ ለማስፋት በባለሀብቱ የሚነሱ የመልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ እንደሚሰራ አስታውቀዋል።
የሀበሻ ፕላውድ ማን ፋክቸሪ ስራ አስኪያጅ አቶ ደሳለኝ ምህረት እንዳሉት፤በግማሽ ቢሊዮን ብር ወጪ የገነባው የእንጨት ውጤቶች ማቀነባበሪያ ፋብሪካ በቀን ተኪ ምርት በማምረት የውጪ ምንዛሬን ለማስቀረት የሚያግዝ ነው።
የዋን የማንፋክቸሪይግ ስራ አስኪያጅ አቶ መላኩ ክንፈ በበኩላቸው፥ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ በመገንባት አሁን ላይ ከ100 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፍጠሩን ተናግረዋል።
አዲስ አበባ፤መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ከሀገራዊ ጥቅም ባለፈ ለዓለም አቀፍ የንግድ መስመር ደህንነትን ...
Apr 8, 2026
ዲላ ፤ መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦የለውጥ ዓመታቱን ጉዞ ስንዘክር ያስመዘገብናቸውን ስኬቶች በማስቀጠል መሆን አለበት ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ር...
Apr 8, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ንግድና ኢንቨስትመንት ስኬት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ተግባራዊ ውጤት ማሳያ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ...
Mar 27, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የብዝኅ ኢኮኖሚ ልማት የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ አህጉራዊ የኢንቨስትመንት ማዕከልነትን እያረጋገጠ ...
Mar 26, 2026