
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 16/2017(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ ለቴክኖሎጂ ሽግግርና ባለሙያን ለማብቃት ከብራዚል ጋር ተቀራርባ የምትሰራበት አቅጣጫ መቀመጡን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት በብራዚል ሳኦ ፓውሎ ግዛት የሚገኙ የተለያዩ ኩባንያዎችን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተን ስኬታማ ውይይቶችን አድርገናል ብለዋል።
የንግድ፣ ወታደራዊና የግብርና ዘርፍ የሚደግፉ አውሮፕላኖችን አምራች የሆነውን ኢምብሬር (Embraer) ኩባንያን ጎብኝተናል ያሉት አቶ ተመስገን ኩባንያው በአቪዬሽን ኢንዱስትሪ ዘርፍ በሀገራችን ከሚገኙ ተቋማት ጋር በትብብርና በጋራ የመስራት ፍላጎት እንዳለው ተገንዝበናል ብለዋል።

የሳኦ ጆዜ ዶስ ካምፖስ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ፓርክ ሌላኛው ጉብኝት ያደረጉበት ተቋም መሆኑን ገልጸው የቴክኖሎጂ ፓርኩ የፈጠራ ሃሳብን ለለውጥና ችግር ፈች መፍትሄ በሚያመጡ ስታርት አፖች፣ መካከለኛና ከፍተኛ የተግባር ተኮር ስራዎች ዙሪያ በዓለም አቀፍ ደረጃ በተዘረጋ የዘርፉ ስራ ሂደት ያለው ተሳትፎ ሰፊ መሆኑን ጠቁመዋል።
ዲጂታል ኢትዮጵያ ርዕይን ዕውን ለማድረግ በፈጠራና ቴክኖሎጂ የታገዘ ስራን መተግበር የጀመረችው ኢትዮጵያ ከመሰል ተቋማት ጋር በጋራ የመስራት መርህ ትከተላለች ብለዋል።

የብራዚሉ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ፓርክ የኢትዮጵያ መንግስት ለቴክኖሎጂና ፈጠራ የሰጠውን ትኩረት አድንቋል ሲሉም ገልጸዋል።
በቀጣይ በቴክኖሎጂ ሽግግርና ባለሙያን ማብቃት ላይ ተቀራርበን የምንሰራባቸውን አቅጣጫዎች አስቀምጠናል ብለዋል።
አዲስ አበባ፤መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ከሀገራዊ ጥቅም ባለፈ ለዓለም አቀፍ የንግድ መስመር ደህንነትን ...
Apr 8, 2026
ዲላ ፤ መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦የለውጥ ዓመታቱን ጉዞ ስንዘክር ያስመዘገብናቸውን ስኬቶች በማስቀጠል መሆን አለበት ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ር...
Apr 8, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ንግድና ኢንቨስትመንት ስኬት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ተግባራዊ ውጤት ማሳያ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ...
Mar 27, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የብዝኅ ኢኮኖሚ ልማት የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ አህጉራዊ የኢንቨስትመንት ማዕከልነትን እያረጋገጠ ...
Mar 26, 2026