
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 5/2017(ኢዜአ)፡- የልማት ፍላጎትን በሀገር ውስጥ ገቢ ለማሟላት ዘርፉን በቴክኖሎጂ መደገፍና የህዝቡን ተሳትፎ ማሳደግ እንደሚገባ የገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ ገለጹ።
ከተለያዩ የዓለም ሀገራት የመጡ የታክስ አመራሮች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም(አይ ኤም ኤፍ) እና የዓለም ባንክ ተወካዮች በተገኙበት ለሶስት ቀናት በአዲስ አበባ ሲካሄድ የነበረው የሀገር ውስጥ ገቢ አሰባሰብ ላይ ያተኮረው ጉባኤ ዛሬ ተጠናቋል፡፡

ከጉባኤው መጠናቀቅ በኋላ ተሳታፊዎች የአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከልና የዓድዋ ድል መታሰቢያን ጨምሮ በአዲስ አበባ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
የገቢዎች ሚኒስትር አይናለም ንጉሴ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት፤ የመካከለኛ ዘመን የገቢ አሰባሰብ ስትራቴጂ የቀረጹና ወደ ስራ የገቡ ሀገራት ውጤታማ መሆን ችለዋል።
ኢትዮጵያ የገቢ መሰብሰብ አቅሟን ለማሳደግ በተያዘው ዓመት የመካከለኛ ዘመን የገቢ አሰባሰብ ስትራቴጂ ቀርጻ ወደ ስራ ገብታለች ብለዋል።
የልማት ፍላጎትን በሀገር ውስጥ ገቢ ለማሟላት ዘርፉን በቴክኖሎጂ መደገፍና የህዝብን ተሳትፎ ማሳደግ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

ጉባኤው በሀገር ውስጥ ገቢ አሰባሰብ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችና የመፍትሔ ርምጃዎችን መውሰድ የሚያስችል የልምድ ልውውጥ መደረጉንም አንስተዋል፡፡

የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ክላራ ሚራ የአፍሪካ ሀገራት በገቢ አሰባሰብ ሂደት መሻሻል እያሳዩ ቢሆንም ካለው አህጉራዊ አቅም አንፃር የሚሰበሰበው ገቢ በቂ አይደለም ብለዋል፡፡
በመሆኑም ተቋሙ የሀገራቱን የውስጥ ገቢ አሰባሰብ አቅም ለማሳደግ የሚያደረገውን የቴክኒክና ሙያዊ ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡

በማላዊ ገቢዎች ሚኒስቴር የፖሊሲ ጥናትና ምርምር ምክትል ዳይሬክተር ማሳ ሳማንታ ኢትዮጵያ በራሷ የገቢ አቅም ትልልቅ የልማት ሥራዎችን እያከናወነች መሆኑን መመልከታቸውን ተናግረዋል፡፡
በአዲስ አበባ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች አበረታችና ልምድ ሊወሰድባቸው የሚገባቸው መሆናቸውን ገልጸው፤ ይህም ከፍተኛ የሥራ ዕድል በመፍጠር የጎላ አበርክቶ ይኖራቸዋል ነው ያሉት፡፡
አዲስ አበባ፤መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ከሀገራዊ ጥቅም ባለፈ ለዓለም አቀፍ የንግድ መስመር ደህንነትን ...
Apr 8, 2026
ዲላ ፤ መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦የለውጥ ዓመታቱን ጉዞ ስንዘክር ያስመዘገብናቸውን ስኬቶች በማስቀጠል መሆን አለበት ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ር...
Apr 8, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ንግድና ኢንቨስትመንት ስኬት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ተግባራዊ ውጤት ማሳያ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ...
Mar 27, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የብዝኅ ኢኮኖሚ ልማት የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ አህጉራዊ የኢንቨስትመንት ማዕከልነትን እያረጋገጠ ...
Mar 26, 2026