የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
የአፍሪካ ህብረት

ኢትዮጵያ በስታርታአፕ ዘርፍ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሚያደርጋትን ስነ-ምህዳር እየገነባች ነው

Mar 12, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤መጋቢት 2/2017(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በስታርታአፕ ዘርፍ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ የሚያደርጋትን ስነ-ምህዳር እየገነባች እንደምትገኝ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ (ዶ/ር) ገለጹ።


የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኮሪያ ዓለም ዓቀፍ ተራድኦ ድርጅት (ኮይካ) ጋር በመተባበር የስታርታፕ ዲጂታል አማራጭ ዲዛይን ምዕራፍ የተመለከተ አውደ ጥናት አካሄዷል።


በአውደ ጥናቱ ላይ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ (ዶ/ር) ፣ በኢትዮጵያ የኮሪያ ዓለም ዓቀፍ ተራድኦ ድርጅት ምክትል ዳይሬክተር ያንግሺን ፓርክ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።


ማዕቀፉ የኢትዮጵያን የጀማሪ የስራ ፈጠራ (ስታርታፕ) ዘርፍ ከሀገር አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ማድረግ የሚያስችል ምቹ ስነ-ምህዳር መፍጠርን ያለመ ነው።


የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ባይሳ በዳዳ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የስታርታፕ መድረክ ተወዳዳሪ ለማድረግ የሚያስችል ስነ-ምህዳር ለመገንባት እየሰራች እንደምትገኝ አመልክተዋል።


ስታርታፕ ፈጣን የሀገር ኢኮኖሚ ማበልፀጊያ ሞተር ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው የኢትዮጵያ ስታርታፕ ዲጂታል ፕላትፎርም ዘርፉን ለማሳደግ እና ኢኮኖሚውን የመደገፍ ፋይዳ አለው ብለዋል።


መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ትኩረት ብዙ ሀብት ማፍራት የቻሉ ወጣቶች እና ዜጎች ተፈጥረዋል ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው።


በኢትዮጵያ የኮሪያ አለም ዓቀፍ ተራድኦ ድርጅት ምክትል ዳይሬክተር ያንግሺን ፓርክ (ካይካ) ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ በስታርታፕ ዘርፍ ላይ የምታደርገውን የስነ-ምህዳር ግንባታ ስኬታማ እንዲሆን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አመልክተዋል።


ኮይካ ኢትዮጵያ በዘርፉ ለምታከናውናቸው ስራዎች ድጋፍ እንደሚያደርግ መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ቀጣናዊ ደኅንነትን በማስጠበቅ ለጋራ ብልፅግና ወሳኝ ነው

አዲስ አበባ፤መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ከሀገራዊ ጥቅም ባለፈ ለዓለም አቀፍ የንግድ መስመር ደህንነትን ...

Apr 8, 2026

የለውጥ ጉዟችንን ስንዘክር ያስመዘገብናቸውን ስኬቶች በማስቀጠል ነው

ዲላ ፤ መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦የለውጥ ዓመታቱን ጉዞ ስንዘክር ያስመዘገብናቸውን ስኬቶች በማስቀጠል መሆን አለበት ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ር...

Apr 8, 2026

የኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ስኬት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ተግባራዊ ውጤት ማሳያ ነው

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ንግድና ኢንቨስትመንት ስኬት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ተግባራዊ ውጤት ማሳያ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ...

Mar 27, 2026

የኢትዮጵያ የብዝኅ ኢኮኖሚ ልማት የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ የኢንቨስትመንት ማዕከልነት እያረጋገጠ ነው

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የብዝኅ ኢኮኖሚ ልማት የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ አህጉራዊ የኢንቨስትመንት ማዕከልነትን እያረጋገጠ ...

Mar 26, 2026