
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የኢንተርፕርነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት የኢንተርፕርነርሺፕ ስነ-ምህዳር ግንባታ ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባው የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል አስገነዘቡ።
ሚኒስቴሩ የኢንተርፕርነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩትን የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት አፈፃፀም ገምግሟል፡፡
በዚህ ወቅት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል እንደገለጹት፣ ኢንስቲትዩቱ ምሳሌ የሚሆን አካታችነትንና በብዙ እጥፍ ያደገ ተደራሽነትን አሳይቷል፡፡

በተለይም በክህሎት ልማትና በሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ ከፍተኛ መነቃቃትን በመፍጠር የሚታዩ ውጤቶችን ማስመዝገብ ችሏል ብለዋል፡፡
በቀጣይ የኢንተርፕርነርሺፕ ስነ-ምህዳር ግንባታ ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባው ሚኒስትሯ መጠቆማቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
በክህሎት ልማቱ ላይ ያለውን የአሰለጣጠን ዘይቤ ፈጠራ የታከለበት እንዲሆን ማድረግ እና የኢንተርፕራይዝ ምስረታ ከልማዳዊ አሠራሮች የተላቀቀና ክፍተቶችን የሚሞላ አድርጎ መቃኘት ላይ በትኩረት እንዲሰራ አቅጣጫ ማስቀመጣቸውም በመረጃው ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም የቱሪዝም ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የሥራ አፈፃፀምም ተገምግሟል፡፡
ኢንስቲትዩቱ የጀመራቸው የሪፎርም ተግባራት ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገልጸዋል፡፡
በቱሪዝም ዘርፍ የሰለጠነ የሰው ሃይል አቅርቦትና ፍላጎት ያለመጣጣም በመኖሩ ነባራዊ ሁኔታውን ያገናዘበና የበይነ መረብ የሥልጠና አማራጮችንም ጭምር የሚጠቀም የሰው ኃይል ልማት ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡
በዘርፉ በልምድ የተገኘ ሙያን ቴክኒካዊና ባህሪያዊ ብቃቶችን መዝኖ እውቅና መስጠት ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባም አመላክተዋል።
ከእንግሊዘኛ በተጨማሪ በሌሎች የውጭ ቋንቋዎች ሥልጠና ላይ የተጀመሩ ሥራዎችን ማጠናከር ይገባል ነው ያሉት፡፡
የባህል ምግቦችን በጥናት ለይቶ ወደ ሆቴሎች ሜኑ ለማስገባት የተጀመሩ ሥራዎች ባህሉን ከመጠበቅ ባሻገር ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠርና አካባቢያዊ ኢኮኖሚውን ለማነቃቃት ከፍተኛ ፋይዳ ያለው በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አመላክተዋል፡፡
አዲስ አበባ፤መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ከሀገራዊ ጥቅም ባለፈ ለዓለም አቀፍ የንግድ መስመር ደህንነትን ...
Apr 8, 2026
ዲላ ፤ መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦የለውጥ ዓመታቱን ጉዞ ስንዘክር ያስመዘገብናቸውን ስኬቶች በማስቀጠል መሆን አለበት ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ር...
Apr 8, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ንግድና ኢንቨስትመንት ስኬት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ተግባራዊ ውጤት ማሳያ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ...
Mar 27, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የብዝኅ ኢኮኖሚ ልማት የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ አህጉራዊ የኢንቨስትመንት ማዕከልነትን እያረጋገጠ ...
Mar 26, 2026