
አዲስ አበባ፤የካቲት 10/2017(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በኤሌክትሪክ ኃይል ልማት ምስራቅ አፍሪካን ለማስተሳሰር በትኩረት እየሰራች መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ፡፡
ኢትዮጵያ በኤሌክትሪክ ኃይል ልማት ምስራቅ አፍሪካን ለማስተሳሰር በትኩረት እየሰራች መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ፡፡
ስምንተኛው የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም “ከእመርታ ወደ ብልጽግና፤ የአፍሪካን ቀጣናዊ የእሴት ሰንሰለቶች አቅም ማጠናከር” በሚል መሪ ሀሳብ በአፍሪካ የኢኮኖሚክ ኮሚሽን ተካሂዷል፡፡
የቢዝነስ ፎረሙ በአፍሪካ የቁም እንስሳት፣ግብርና እና ፋርማሲዩቲካል ዘርፎች ቀጣናዊ የእሴት ሰንሰለት እና ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ልማት ላይ ያተኮረ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡
በፎረሙ ላይ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፤ የአየር ንብረት ለውጥን እና አደጋን መቋቋም የሚችል መሰረት ልማት ማስፋፋት ለዘርፉ መነቃቃት ቁልፍ ጉዳይ መሆኑንም አንስተዋል።
ኢትዮጵያ በስንዴ ልማት ያካሄደችው አብዮት ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ መሆን የሚችል መሆኑን አንስተው፥ በቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍም ጠንካራ ሥራዎችን በመስራት ላይ እንደምትገኝ ጠቁመዋል፡፡
በአፍሪካ የማምረት አቅምን በማሳደግ ለውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታዎች መፍጠር ላይ ትኩረት ሊደረጉ እንደሚገባም ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በርካታ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመገንባት ኢንቨስተሮችን በመሳብ ላይ እንደምትገኝ ጠቁመው፥ በጨርቃጨርቅ ዘርፍ አመርቂ ስራዎች መስራቷንም ገልጸዋል፡፡
በቅርቡ ያካሄደችው የኢኮኖሚ ሪፎርም የኢንቨስትመንት ፍላጎት እንዲጨምር በማድረግ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ መነቃቃትን እንደፈጠረም ነው የጠቆሙት።
ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል ልማት ምስራቅ አፍሪካን ለማስተሳሰር እየሰራች መሆኑንም አንስተዋል፡፡
ኢትዮጵያ በኃይል ልማት ቀጣናውን ለማስተሳሰር ጥረት እያደረገች ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፤ የታላቁ ህዳሴና የኮይሻ የታዳሽ ኤሌክትሪክ ማምንጫ ግድቦች ለዚህ ማሳያ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።
የአፍሪካን አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለማሳደግ ለፈጠራ እንዲሁም ለስራና ክህሎት ትምህርት ትኩረት መስጠት እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ሥራ አስፈፃሚ ክላቨር ጌቴቴ በበኩላቸው፥ በአህጉሪቱ እሴትን በመጨመር የሚሰሩ ስራዎንችን ማሳደግ የወጣቶችን የስራ ዕድል ፈጠራ ማጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
በአህጉሪቱ የመድኃኒት ምርት አቅርቦትን በማሳደግ እንዲሁም በሌሎችም የማምረት አቅምን በማጠናከር ለኢኮኖሚው መረጋጋትና ዕድገት መስራት እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡
የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ-መንበር ሞኒክ ንሳንዛባጋንዋ (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ የአፍሪካ ህብረት 2063 አጀንዳን ለማሳካት አለም አቀፋዊ እና አህጉራዊ የእሴት ሰንሰለቶችን በሚያጎለብቱ ዕቅዶች ዙሪያ ትልቅ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣናዎች መጠናከር እንዳላባቸው የጠቆሙት ምክትል ሊቀመንበሯ ለስራ እድል ፈጠራ፣ ለኢንዱስትራላይዜሽን መስፋፋት ብሎም ለእሴት ሰንሰለት መጨመር ትልቅ ሚና ያለው መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡
ፎረሙን በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ከአፍሪካ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን እና ከአረብ ባንክ ፎር ኢኮኖሚክ ዴቨሎፕመንት ጋር በመተባበር እንዳዘጋጁት ተገልጿል።
የአፍሪካ የቢዝነስ ፎረም እ.አ.አ ከ2018 ጀምሮ በየዓመቱ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
አዲስ አበባ፤መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ከሀገራዊ ጥቅም ባለፈ ለዓለም አቀፍ የንግድ መስመር ደህንነትን ...
Apr 8, 2026
ዲላ ፤ መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦የለውጥ ዓመታቱን ጉዞ ስንዘክር ያስመዘገብናቸውን ስኬቶች በማስቀጠል መሆን አለበት ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ር...
Apr 8, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ንግድና ኢንቨስትመንት ስኬት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ተግባራዊ ውጤት ማሳያ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ...
Mar 27, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የብዝኅ ኢኮኖሚ ልማት የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ አህጉራዊ የኢንቨስትመንት ማዕከልነትን እያረጋገጠ ...
Mar 26, 2026