
ታርጫ ፣የካቲት 5/2017 (ኢዜአ):- በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በግንባታ ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶች በፍጥነት እንዲጠናቀቁ የክልሉ ምክር ቤት አባላት ጠየቁ።
የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፤ በበኩላቸው የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት ለማከናወን በልዩ ትኩረት ይሰራል ብለዋል።
ዛሬ በተጠናቀቀው የክልሉ ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔ የምክር ቤቱ አባላት ጥያቄና አስተያየቶች አንስተው ምላሽ ተሰጥቷል።

ከምክር ቤቱ አባላትም የተለያዩ ጥያቄና አስተያየቶች ተነስተው የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) እና በሚመለከታቸው አስፈፃሚ አካላት ምላሽና ማብራሪያ እየተሰጠ ነው።
በተለያዩ አካባቢዎች የተጀመሩ የግንባታ ፕሮጀክቶች በፍጥነት እንዲጠናቀቁ ቀጣይ ትኩረት እንዲደረግ ከምክር ቤቱ አባላት ተነስቷል።
ከምክር ቤቱ አባላት መካከል አቶ አማረ ብርሃኑ፤ ውጤታማ የሆኑ ጅምር የልማት ስራዎችና ሌሎችም ክልላዊ እንቅስቃሴዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀው የሁላችንም ድጋፍና ርብርብ ያስፈልጋል ሲሉም አስገንዝበዋል።
በተለይም በአንዳንድ አካባቢዎች ተጀምረው ያልተጠናቀቁ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች እንዲፋጠኑ የተበላሹትም እንዲጠገኑ ትኩረት ይሻል ብለዋል።
ሌላኛዋ የምክር ቤት አባል ወ/ሮ ከበቡሽ ከበደ፤ በተለይም በክረምት ወቅት ለህብረተሰቡ እንቅስቃሴ ችግር እየፈጠሩ ያሉ የመንገድ ፕሮጀክቶች በአፋጣኝ እልባት እንዲያገኙ ጠይቀዋል።
የመጠጥ ውሃና ሌሎችም በጅምር ላይ የሚገኙ ፕሮጀክቶች በፍጥነት እንዲጠናቀቁ አስፈፃሚው አካል በልዩ ትኩረት እንዲሰራ የምክር ቤቱ አባላት አሳስበዋል።
የክልሉ ምክትል ርእሰ መስተዳድር ኢንጅነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፤ በግንባታ ላይ ያሉ ፕሮጀከቶች ግንባታ እንዲፋጠን በልዩ ትኩረት የሰራል ብለዋል።
የመጠጥ ውሃ ተደራሽነትን ለማስፋት ሰፊ ጥረት መደረጉንና እየተደረገም መሆኑን አንስተው ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አረጋግጠዋል።
የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በተመለከተም ህብረተሰቡን በማሳተፍ የግንባታና ጥገና ስራዎች መከናወናቸውን አንስተው በቀጣይም ብዙ ስራ ይጠብቀናል ብለዋል።
በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ ፋጂዮ ሳፒ፤ የመንገድ ግንባታና ጥገና ስራዎች በተጠናከረ መልኩ የሚቀጥሉ ይሆናል ብለዋል።
ከፍተኛ በጀት የሚጠይቁ የድልድይና የመንገድ ልማት ፕሮጀክቶች ግንባታም በሂደት የሚሰሩ መሆኑን አረጋግጠዋል።
አዲስ አበባ፤መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ከሀገራዊ ጥቅም ባለፈ ለዓለም አቀፍ የንግድ መስመር ደህንነትን ...
Apr 8, 2026
ዲላ ፤ መጋቢት 29/2018 (ኢዜአ)፦የለውጥ ዓመታቱን ጉዞ ስንዘክር ያስመዘገብናቸውን ስኬቶች በማስቀጠል መሆን አለበት ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ር...
Apr 8, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ንግድና ኢንቨስትመንት ስኬት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ተግባራዊ ውጤት ማሳያ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ...
Mar 27, 2026
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የብዝኅ ኢኮኖሚ ልማት የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማሳደግ አህጉራዊ የኢንቨስትመንት ማዕከልነትን እያረጋገጠ ...
Mar 26, 2026