አዲስ አበባ፤ ጥር 12/2017(ኢዜአ)፡- በሐዋሳ ከተማ የተሰራው የኮሪደር ልማት የሞተር አልባ ትራንስፖርትን ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ መጠቀም አስችሎናል ሲሉ የሐዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ።
አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የከተማዋ ነዋሪዎች እንደገለጹት በከተማዋ በኮሪደር ልማት የተገነባው መሰረተ ልማት ሞተር አልባ ትራንስፖርት ዳግም እንዲያንሰራራ አድርጓል።
ሻምበል መሰለ ስንታየሁ አስተያየት ከሰጡ ነዋሪዎች መካከል ሲሆኑ የኮሪደር ልማቱ የከተማዋን ገፅታ መቀየሩን ጠቅሰው፥ ለብስክሌት ተለይቶ የተሰራው መንገድም ያለምንም ስጋት ለማሽከርከር እንዳስቻላቸው አንስተዋል።
ይሁን እንጂ የብስክሌት መንገድ አጠቃቀም ላይ ክፍተት መኖሩን አልፎ አልፎ እግረኞች ወደ መንገዱ እንደሚገቡ በማሳያነት ገልጸው፥ ችግሩን ለመቅረፍ ግንዛቤ መፍጠር ይገባል ብለዋል።
ሌላኛው የከተማዋ ነዋሪ አማኑኤል ፈረደ ከዚህ ቀደም ብስክሌት ሲያሽከረክር የሚጠቀመው ከሌሎች ተሽከሪካሪዎች ጋር በአንድ መስመር ላይ መሆኑን አውስቶ፤ ይህም ለአደጋ አጋላጭ ነበር ሲል ገልጿል።
የብስክሌት መንገድ ለብቻ በመሰራቱ ደህንነቱ የተጠበቀና ምቹ ሁኔታ እንደፈጠለት ተናግሯል።
አቶ ወንድወሰን ታደሰ በበኩላቸው፥ የብስክሌት መንገዱ ለሐዋሳ ድምቀትን የፈጠረ መሆኑን ጠቅሰው፥ በሌሎች የከተማዋ አካባቢዎች መስፋፋት እንዳለበት አመላክቷል።
በሐዋሳ ከተማ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ሃላፊ አቶ መብራቱ ገብሬ እንደተናገሩት፥ የኮሪደር ልማት ስራው በከተማዋ የብስክሌት ተጠቃሚዎች ቁጥር እንዲጨምር አድርጓል።
በብስክሌት የሚደረግ ጉዞ ጭስ አልባ በመሆኑ የአየር ብክለትን ለመቀነስ እንዲሁም የማህበረሰቡን ጤና በመጠበቅ ረገድ የጎላ አስተዋፅኦ አለው ብለዋል።
መንግስትም ይህን ከግንዛቤ በማስገባት በኮሪደር ልማት ሥራዎች ለብስክሌት መንገድ ትኩረት ሰጥቷል ነው ያሉት።
የኮሪደር ልማቱ ምቹ የትራንስፖርት መሰረተ ልማትን ለማስፋፋት ትልቅ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 21/2017(ኢዜአ)፡- የምግብ ዋስትና እና ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ለነገ የሚተው የምርጫ ጉዳይ ባለመሆኑ በልዩ ትኩረት መረባረብ እንደሚገባ...
Feb 28, 2025
ሐረር፤ የካቲት 16/2017(ኢዜአ)፦ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ስራዎች የህዝቡን ተጠቃሚነት ያሳደጉ መሆናቸውን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አ...
Feb 24, 2025
አዲስ አበባ፤ ጥር 30/2017(ኢዜአ)፦የየካቲት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር በነበረበት የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስ...
Feb 8, 2025