🔇Unmute
ሐረር፤ ሚያዝያ 28/2018(ኢዜአ)፦ በሐረር የሳተላይት የመገኛ መረጃ መቀበያ ጣቢያ ተከላ ስራ ተጀምሯል።
የሳተላይት የመገኛ መረጃ መቀበያ ጣቢያ ተከላ ስራውን የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) አስጀምረውታል።
ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በዚሁ ጊዜ የሳተላይት የመገኛ መረጃ መቀበያ ጣቢያው በክልሉ ለሚከናወኑ የልማት ስራዎች ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል ብለዋል።
በተለይም ትክክለኛ የመረጃ ግብዓት ከመስጠት አኳያ ፋይዳው የጎላ መሆኑንም አመልክተዋል።
የተከላ ስራው በአጭር ጊዜ እንዲከናወን የክልሉ መንግስት እገዛ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
የስፔስ ሳይንስና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሪክተር በላቸው ፀሐይ፤ ቴክኖሎጂው መረጃን በከፍተኛ ፍጥነትና ጥራት ተደራሽ ለማድረግ የላቀ ፋይዳ አለው ብለዋል።
እንዲሁም 35 ኪሎ ሜትር ራድየስን በመሸፈን ትክክለኛ ልኬት የሚወስድና 24 ሰዓት የሚሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
የሳተላይት የመገኛ መረጃ መቀበያ ጣቢያው የመንገድ ዲዛይን፣ አጠቃላይ የኮንስትራክሽን ስራ ለሚያከናውኑ፣ የመሬት አጠቃቀምን በጥንቃቄ ለመቆጣጠር፣ ለይዞታ መረጋገጫና ለሌሎችም መረጃን መስጠት የሚያስችል ነው ብለዋል።
የሳተላይት የመገኛ መረጃ መቀበያ ጣቢያ ተከላው በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ መሆኑንም ተናግረዋል።
ጋቼኖ ፤ ግንቦት 12/2018(ኢዜአ)፦ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን የሰላም፣ የልማትና የመቻቻል ተምሳሌት ለማድረግ የህዝቡን አቅም አቀናጅቶ መጠቀም እንደሚገባ የክ...
May 21, 2026
አሶሳ፤ ሚያዝያ 20/2018(ኢዜአ)፦ ከስልጠናው ያገኘነው እውቀት ወቅቱ የሚጠይቀውን ብቁ የህብረት ስራ ማህበራትን ለመፍጠር ያግዘናል ሲሉ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክ...
Apr 29, 2026
ባህርዳር ፤ሚያዝያ 6/2018(ኢዜአ)፡- የአማራ ክልል በቴክኖሎጂ የታገዘ የገቢ አሰባሰብ ስርአትን በመተግበር ረገድ የተገኘው ውጤት ልምድና ተሞክሮ የሚወሰድበት...
Apr 15, 2026
ሮቤ፣ ሚያዝያ 5/2018 (ኢዜአ)፦ የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ዝንባሌ ያላቸው ተማሪዎችን ለተሻለ ውጤት ማብቃት የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወ...
Apr 14, 2026