የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

በዓለም አቀፍ ወቅታዊ ሁኔታዎች ምክንያት የነዳጅ አቅርቦት ላይ የዋጋ ማስተካከያ ተደርጓል-የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር

Apr 3, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፣መጋቢት 24/2018 (ኢዜአ) ፦በመካከለኛው ምስራቅ የተከሰተውን ጦርነት ተከትሎ የዓለም የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ በመጨመሩ የዋጋ ማስተካከያ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ያወጣው ሙሉ መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል፦

በዓለም አቀፍ ወቅታዊ ሁኔታዎች ምክንያት የተከሰተው የነዳጅ አቅርቦትና የዋጋ ማስተካከያን ይመለከታል

በመካከለኛው ምስራቅ የተከሰተውን ጦርነት ተከትሎ ከየካቲት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የዓለም የነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል፡፡

ሁኔታው ከቀን ወደ ቀን ይሻሻላል ተብሎ ቢጠበቅም ነገሮች በመካረራቸው ምክንያት በነዳጅ አቅርቦት ላይ እጥረት ከመፈጠሩም በላይ የአንዳንድ የነዳጅ ምርቶች ዋጋ በከፍተኛ መጠን ሊጨምር ችሏል፡፡

ኢትዮጵያ ከውጭ አስገብታ የምትጠቀማቸው የነዳጅ አይነቶች ነጭ ናፍጣ፣ ቤንዚን፣ የአውሮፕላን ነዳጅ፣ ኬሮሲን፣ ከባድ ጥቁር ናፍጣ እና ቀላል ጥቁር ናፍጣ ሲሆኑ የግዥ ሂደቱም በመንግስትና መንግስት ስምምነት እንዲሁም በዓለም አቀፍ ግልጽ ጨረታ የሚከናወን ነው፡፡

ከመንግስት ጋር በተደረገው ስምምነት መሰረት ስልሳ በመቶ ነጭ ናፍጣ እና መቶ በመቶ የአውሮፕላን ነዳጅ ከኩዌት መንግስት የሚገዛ ሲሆን ቀሪው አርባ በመቶ ነጭ ናፍጣ እንዲሁም መቶ በመቶ ቤንዚንና ጥቁር ናፍጣዎች በጨረታ የሚቀርቡ ናቸው፡፡

ከኩዌት ጋር ያለው ኮንትራት ከጃንዋሪ አንድ ቀን ሁለት ሺህ ሃያ ስድስት እስከ ዲሴምበር ሰላሳ አንድ ቀን ሁለት ሺህ ሃያ ስድስት የሚዘልቅ ሲሆን ከመጫኛ ወደብ እስከ ጅቡቲ ድረስ ያለው የሎጂስቲክስ ዋጋ ወይም ፕሪሚየም ለሁለቱም ምርቶች በበርሜል 9.25 ዶላር ሆኖ በየዓመቱ በሚደረግ ድርድር የሚወሰን ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት በጨረታ አሸናፊ የሆነው ቪቶል የተባለው ኩባንያ ለነጭ ናፍጣ 13.99 ዶላር እንዲሁም ለቤንዚን 10.99 ዶላር ፕሪሚየም በማስከፈል በ360 ቀናት ዱቤ እያቀረበ ይገኛል፡፡

ይህም ማለት የነዳጅ ዋጋ የሚሰላው የወሩ የዓለም አማካይ ዋጋ ላይ ፕሪሚየሙ ተደምሮ ነው፡፡ ለምሳሌ በየካቲት ወር የኩዌት ነጭ ናፍጣ ወርሃዊ አማካይ 86.03 ዶላር ሲሆን ከፕሪሚየሙ ጋር ተደምሮ 95.28 ዶላር ሆኗል፡፡

ሆኖም በጦርነቱ ምክንያት የኩዌት አቅርቦት በመዘጋቱ ለአጣዳፊ ግዥ በወጣው ጨረታ የተገኘው ፕሪሚየም ለአውሮፕላን ነዳጅ 86.33 ዶላር እንዲሁም ለነጭ ናፍጣ 92.88 ዶላር በበርሜል በመሆኑ ዋጋው እጅግ እንዲንር አድርጎታል፡፡

የዓለም አንድ አምስተኛ ድፍድፍ ነዳጅ የሚተላለፍበት የሆርሙዝ የባህር ሰርጥ በመዘጋቱ እንደ ሳዑዲ አረቢያ፣ ኩዌት፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና ኢራቅ ያሉ ሀገራት በቀን የሚያቀርቡት 140 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ ተቋርጧል፡፡

በዚህም ምክንያት ወደ ሀገራችን ይገባ የነበረ 120 ሺህ ሜትሪክ ቶን ነጭ ናፍጣ እና 60 ሺህ ሜትሪክ ቶን የአውሮፕላን ነዳጅ የጫኑ ሶስት መርከቦች በአረብ ባህረ ሰላጤ ላይ ቆመው ይገኛሉ፡፡

መንግስት መደበኛ አቅርቦቱ እንዳይቋረጥ ከተባራሪ ገበያ ወይም በከፍተኛ ዋጋ በመግዛት ለማቅረብ ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ ሆኖም በመንግስት ላይ ያለው የድጎማ ጫና ከ272 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል፡፡

ባለፈው ሳምንት በወጣው ታሪፍ ነጭ ናፍጣ በ139.84 ብር ሲሸጥ መንግስት 95 ብር ይደጉም ነበር፤ ቤንዚንም በ132.18 ብር ሲሸጥ 42 ብር ድጎማ ይደረግለት ነበር፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ድጎማውን በነበረበት መቀጠል አስቸጋሪ በመሆኑ አዲስ የዋጋ ማስተካከያ ተደርጓል፡፡

በዚህም መሰረት አዲሱ የሊትር የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ቤንዚን 142.21 ብር፣ ኬሮሲን 151.39 ብር፣ ነጭ ናፍጣ 163.09 ብር፣ ቀላል ጥቁር ናፍጣ 163.98፣ ከባድ ጥቁር ናፍጣ 160.68 ብር እንዲሁም የአውሮፕላን ነዳጅ 150.48 ብር ሆኗል፡፡ የቀጥታ ተጠቃሚዎች የነጭ ናፍጣ መሸጫ ዋጋ ደግሞ 210 ሆኖ ተደንግጓል፡፡

መንግስት አሁንም ቢሆን በአንድ ሊትር ነጭ ናፍጣ ላይ 71 ብር እንዲሁም በቤንዚን ላይ 32 ብር ድጎማ እያደረገ ይገኛል፡፡ ይህ ድጎማ ባይኖር ኖሮ የናፍጣ ዋጋ 234.17 ብር እንዲሁም የቤንዚን ዋጋ 174.40 ብር ይደርስ ነበር፡፡

አሁንም ቢሆን የሀገራችን የነዳጅ ዋጋ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ሲነፃፀር አነስተኛ ነው፡፡ ለምሳሌ በዶላር ሲሰላ በሀገራችን የናፍጣ ዋጋ 1.032 ዶላር ሲሆን በኬንያ 1.374፣ በጅቡቲ 1.741፣ በታንዛኒያ ደግሞ 1.09 ዶላር ነው፡፡

በአጠቃላይ የቤንዚን የአቅርቦት ችግር የሌለ ሲሆን ነጭ ናፍጣን ጨምሮ ሌሎች የነዳጅ አይነቶች የአቅርቦት እጥረት እና ዋጋ ጭማሪ ቀውስ እስኪስተካከል መንግስት ስርጭቱን የሚከታተልና የሚመራ ቡድን አደራጅቷል፡፡

ቡድኑ በሚያዘጋጀው የአቅርቦትና የስርጭት ቅደም ተከተል የሚቀርበውን ነዳጅ በቁጠባ እና በተቀመጠው የግብይት ስርአት ብቻ እንዲፈፀም ድጋፍና ርብርብ ማድረግም እንደሚገባ መንግስት ያሳስባል፡፡

በቅደም ተከተሉ መሰረትም ነዳጅ የሚያጓጉዙ ቦቴዎች፣ የወጪና ገቢ ምርት ተሽከርካሪዎች፣ የመሰረታዊ ፍጆታና የኤክስፖርት ምርት አምራች ኢንዱስትሪዎች፣ ቁልፍ የመንግስትና የግል የልማት ፕሮጀክቶች፣ መካናይዝድ እርሻዎች፣ የፀጥታና ደህንነት ተቋማት፣ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች፥የጤና አገልግሎቶች፣ የቴሌኮም ታወር ስራዎች፣ የምርጫ ስራዎች፣ የውሃና መብራት አጣዳፊ ስራዎች፣ የሚዲያና ሰብአዊ አገልግሎቶች እንዲሁም ከፍተኛ የተማሪ ቁጥር ያሉባቸው ዩኒቨርሲቲዎች የቅድሚያ አገልግሎት የሚያገኙ ናቸዉ፡፡

ህብረተሰቡ ይህንን አስቸጋሪ ወቅት ለመሻገር በሚደረገው ጥረት ተገቢውን ድጋፍና ትብብር እንዲያደርግ መንግስት ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር

መጋቢት 24 ቀን 2018 ዓ.ም

አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ክልሉን የሰላም፣ የልማትና የመቻቻል ተምሳሌት ለማድረግ የህዝቡን አቅም አቀናጅቶ መጠቀም ይገባል

ጋቼኖ ፤ ግንቦት 12/2018(ኢዜአ)፦ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን የሰላም፣ የልማትና የመቻቻል ተምሳሌት ለማድረግ የህዝቡን አቅም አቀናጅቶ መጠቀም እንደሚገባ የክ...

May 21, 2026

ከስልጠናው ያገኘነው እውቀት ወቅቱ የሚጠይቀውን ብቁ ማህበራትን ለመፍጠር ያግዘናል-ሰልጣኞች

አሶሳ፤ ሚያዝያ 20/2018(ኢዜአ)፦ ከስልጠናው ያገኘነው እውቀት ወቅቱ የሚጠይቀውን ብቁ የህብረት ስራ ማህበራትን ለመፍጠር ያግዘናል ሲሉ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክ...

Apr 29, 2026

በአማራ ክልል በቴክኖሎጂ የታገዘ የገቢ አሰባሰብ ስርዓትን በመተግበር ረገድ የተገኘው ውጤት ልምድ የሚወሰድበት ነው

ባህርዳር ፤ሚያዝያ 6/2018(ኢዜአ)፡- የአማራ ክልል በቴክኖሎጂ የታገዘ የገቢ አሰባሰብ ስርአትን በመተግበር ረገድ የተገኘው ውጤት ልምድና ተሞክሮ የሚወሰድበት...

Apr 15, 2026

መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎችን የፈጠራ ክህሎት ማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወነ ነው

ሮቤ፣ ሚያዝያ 5/2018 (ኢዜአ)፦ የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ዝንባሌ ያላቸው ተማሪዎችን ለተሻለ ውጤት ማብቃት የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወ...

Apr 14, 2026