🔇Unmute
ሀዋሳ፤መጋቢት 24/2018 (ኢዜአ) ፡-የመካከለኛው ምስራቅ ወቅታዊ ሁኔታ በነዳጅ አቅርቦት ላይ የፈጠረውን ችግር ለመቋቋም የተቀመጡ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በአግባቡ ልንተገብር ይገባል ሲሉ ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።
የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በኢትዮጵያ የነዳጅ ግብይትና አቅርቦት ላይ ሊያደርስ የሚችለውን ተጽዕኖ እንዲሁም መንግሥት የሚከተላቸውን የመፍትሄ አቅጣጫዎች በተመለከተ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ሰፊ ማብራሪያ መስጠታቸው ይታወቃል።
በተለይም ነዳጅን በቁጠባ መጠቀም፣ የታዳሽ ኃይል አማራጮችን የመጠቀም ልምድ፣ የእግር ጉዞ ባህልን ማጎልበት፣ የሕዝብ ትራንስፖርትን መጠቀም፣ በነዳጅ ግብይት ላይ የሚስተዋሉ ሕገ-ወጥ ተግባራትን ማጋለጥ እና ሌሎችም ከህብረተሰቡ የሚጠበቁ ዋና ዋና ተግባራት መሆናቸውን ሚኒስትሩ አብራርተዋል።

በዚህም መሰረት የችግሩን ሁኔታ ታሳቢ ያደረገና መፍትሄዎችን ያገናዘበ አሰራር መከተልና መፍትሄውን ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ ሆኗል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ የኢዜአ ሪፖርተር በሀዋሳ ከተማ ተዘዋውሮ ያነጋገራቸው የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፤ በነዳጅ አቅርቦት ላይ የተፈጠረውን ችግር ለመቋቋም የተቀመጡ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በአግባቡ ልንተገብር ይገባል ብለዋል።
ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል አቶ ሃይለየሱስ ወልደሰንበት፤ በመካከለኛው ምስራቅ የተከሰተው ጦርነት በነዳጅና ሌሎችም ከውጭ ሊገቡ በሚችሉ ምርቶች ላይ እጥረት መፈጠሩ የሚጠበቅ ነው ብለዋል።
እንደ ሀገር መፍትሄዎቹ ላይ በማተኮር በመተሳሰብና በመተጋገዝ ጭምር ችግሩን ልናልፈው ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።
በተለይም በነዳጅ አቅርቦት ላይ የተፈጠረውን ችግር ለመቋቋም የተቀመጡ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በአግባቡ ልንተገብር ይገባል ብለዋል።
"እኔ ከ30 ዓመታት በላይ ብስክሌት የማሽከርከር ልምድ አለኝ" ያሉት አቶ ሃይለየሱስ፤ መሰል የትራንስፖርት አማራጮችን መጠቀምና በእግርም የመጓዝ ልምድን እናዳብር ሲሉ ተናግረዋል።፡
ሌላኛው የከተማዋ ነዋሪ አቶ መሳይ ጨርቆስ፤ የመካከለኛውን ምስራቅ ጦርነት ተከትሎ በነዳጅ አቅርቦት ላይ እጥረት መፍጠሩ ሁላችንንም ያሳሰበን በመሆኑ ችግሩን ለማለፍ መፍትሄው ላይ በትብብር መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል።
ለተፈጠረው ወቅታዊ ችግር የተቀመጡ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን መተግበር፣ መተሳሰብና ለአማራጭ መፍትሄዎች መትጋት ያስፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል።
አቶ ቢንያም አበበ በበኩላቸው፤ የነዳጅ አቅርቦት እጥረቱ የሚያስከትለውን ጫና ለመቀነስ መንግስት ያስቀመጣቸው የመፍትሄ አማራጮች ተገቢ መሆናቸውን ገልጸዋል።
በመሆኑም ለተግባራዊነቱ የመንግስት አካላት ቁጥጥር እንዳለ ሆኖ ሁላችንም እንደ ዜጋ የመፍትሄው አካል መሆን ይጠበቅብናል ብለዋል።
በሀዋሳ ታክሲ በማሽከርከር የሚተዳደሩት አቶ ደመላሽ ሞቲ፤ የነዳጅ እጥረቱ ለሁሉም ፈተና ሆኖ የመጣ ችግር ቢሆንም መፍትሄው ላይ ማተኮር የግድ ይለናል ሲሉ ተናግረዋል።
በመሆኑም እጥረቱን ለመቋቋም በመንግስት የተቀመጡ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በአግባቡ ልንተገብር ይገባል ብለዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025