የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

የኮሪደር ልማቱ መልከ-ብዙ ትሩፋቶችን አበርክቷል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Mar 26, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 15/2018 (ኢዜአ)፡- የኮሪደር ልማቱ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ፣ ከባቢያዊ እና ሌሎችም በርካታ ትሩፋቶች ማበርከቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከተማ፣ ከተሜነት፣ ክትመትና የኮሪደር ልማት በተሰኙ ጉዳዮች ላይ ከቃና ቲቪ ጋር ቆይታ አድርገዋል።

በዚሁ ወቅትም፤ የኮሪደር ልማቱ በኢኮኖሚ፣ በሥራ ፈጠራ፣ በክኅሎት፣ በከባቢያዊ ፋይዳ፣ ዓየር ንብረት ጥበቃ እና በማኅበራዊ ግብ ረገድ በርካታ ትሩፋቶች ማበርከቱን አብራርተዋል።

ሥራ አጥነት በማክሮ ኢኮኖሚው አንዱ ስብራት ተብሎ መቀመጡን አውስተው፤ የኮሪደር ልማት እየተሠራም ፕሮጀክቱ ካለቀ በኋላም የሥራ ዕድል መፍጠሩን አስረድተዋል።

በክኅሎት ረገድም የኮሪደር ልማት በርካታ ባለሙያዎች ማፍራቱን ጠቁመው፤ እነዚህ ወጣቶች ዲዛይን ሠርተው የሚያከናውኑት ግንባታ የሚያስደንቅ ነው ብለዋል።

የኮሪደር ልማቱን ተከትሎ በርካታ ቤቶችን በመላ ሀገሪቱ በአጭር ጊዜ ገንብተን እያጠናቀቅን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ እነዚህ ቤቶች የኮሪደር ልማቱ አካል መሆናቸውን አስታውቀዋል።

የኮሪደር ልማቱ የነበረውን የመንገድ መዘጋጋት በመቀነስ የጉዞ ጊዜን ማሳጠር ማስቻሉ ሌላኛው ትሩፋቱ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በቱሪዝም ረገድም ከፍተኛ አስተዋጽዖ ማበርከቱን ጠቅሰው፤ ዘንድሮ ካለፈው ዓመት የበለጠ የቱሪዝም እንቅስቃሴ መኖሩን ጠቅሰዋል።

ንጽህናው የተጠበቀ፣ ያማረ ዘላቂ ሥነ-ምኅዳር መፍጠር በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት ህልም መሆኑን ያደጉትም ያን የመጠበቅ ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸው፤ ስለዚህ ከከባቢያዊ ግብ አኳያ የኮሪደር ልማት ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል ብለዋል።

በንጹህ ከባቢ መኖር በገንዘብ የማንለካቸውን የጤና ትሩፋቶች ያስገኛል፤ ለዓየር ንብረት ጥበቃም ከፍተኛ አስተዋጽዖ አለው ሲሉ አብራርተዋል።

የኮሪደር ልማት ሥራ ሂደቱ ከባድ ውጤቱ ጥሩ መሆኑን በመግለጽ፤ ኮሪደርን ሰዎች ስም ሊያወጡለት ሲሞክሩ መጀመሪያ ግቦቹን ማየት እና ግቦቹን በምን ደረጃ እንዳሳካ ማረጋገጥ እንደሚጠበቅባቸው አመላክተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ክልሉን የሰላም፣ የልማትና የመቻቻል ተምሳሌት ለማድረግ የህዝቡን አቅም አቀናጅቶ መጠቀም ይገባል

ጋቼኖ ፤ ግንቦት 12/2018(ኢዜአ)፦ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልን የሰላም፣ የልማትና የመቻቻል ተምሳሌት ለማድረግ የህዝቡን አቅም አቀናጅቶ መጠቀም እንደሚገባ የክ...

May 21, 2026

ከስልጠናው ያገኘነው እውቀት ወቅቱ የሚጠይቀውን ብቁ ማህበራትን ለመፍጠር ያግዘናል-ሰልጣኞች

አሶሳ፤ ሚያዝያ 20/2018(ኢዜአ)፦ ከስልጠናው ያገኘነው እውቀት ወቅቱ የሚጠይቀውን ብቁ የህብረት ስራ ማህበራትን ለመፍጠር ያግዘናል ሲሉ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክ...

Apr 29, 2026

በአማራ ክልል በቴክኖሎጂ የታገዘ የገቢ አሰባሰብ ስርዓትን በመተግበር ረገድ የተገኘው ውጤት ልምድ የሚወሰድበት ነው

ባህርዳር ፤ሚያዝያ 6/2018(ኢዜአ)፡- የአማራ ክልል በቴክኖሎጂ የታገዘ የገቢ አሰባሰብ ስርአትን በመተግበር ረገድ የተገኘው ውጤት ልምድና ተሞክሮ የሚወሰድበት...

Apr 15, 2026

መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎችን የፈጠራ ክህሎት ማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወነ ነው

ሮቤ፣ ሚያዝያ 5/2018 (ኢዜአ)፦ የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ዝንባሌ ያላቸው ተማሪዎችን ለተሻለ ውጤት ማብቃት የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወ...

Apr 14, 2026