🔇Unmute
ወላይታ ሶዶ ፤ ጥቅምት 1/2018(ኢዜአ):- በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የእንስሳት እርባታን በማዘመን ህብረተሰቡ ከዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆን የተከናወነው ተግባር ውጤት ማምጣቱን የግብርና ሚኒስቴር ገለጸ።
ሀገር አቀፍ የእንስሳት አርቢዎች ቀን በወላይታ ሶዶ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል።
በወቅቱም የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ፍቅሩ ረጋሳ (ዶ/ር)፤ የእንስሳት እርባታን በማዘመን ህብረተሰቡ በሌማት ትሩፋት ተጠቃሚ እንዲሆን የተሰራው ስራ ውጤት አምጥቷል ብለዋል።

በወላይታ ሶዶ ከተማ በተካሄደ የእንስሳት እርባታ ጣቢያዎች የመስክ ምልከታ ላይ ተገኝተው በወተት ላም እርባታ ዘርፍ እየተከናወነ ያለው ተግባር የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር አካል እንደሆነ በመጥቀስ እንቅስቃሴውም አበረታች መሆኑን ገልጸዋል።
በመስክ ምልከታውም በሀገር አቀፍ ደረጃ የተውጣጡ የዘርፉ ተዋንያን እንዲሳተፉ መደረጉን ጠቁመው፤ በወላይታ ሶዶ ከተማ ያዩትን ተሞክሮ በመቀመር የተሻለ እንዲሰሩ ምሳሌ የሚሆን ነው ብለዋል።

በክልሉ በእንስሳት እርባታ ዘርፍ የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ በቁርጠኝነት እየተደረገ ያለው ድጋፍ ውጤት ማሳየቱን አመልክተዋል።
የክልሉን አርሶ እና አርብቶ አደሮችን ኑሮ ለማሻሻል በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የገለጹት ደግሞ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ መሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር) ናቸው።

በተቀናጀ መንገድ ዘርን በድጋፍ መልክ በማቅረብ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገባቸውን ጠቁመው፤ የወላይታ ሶዶ ከተማ እንስሳት አርቢዎች ያስመዘገቡት ውጤት የዚህ ማሳያና በትጋት የመጣ መሆኑን ተናግረዋል።
በሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር መንግስት የጀመረውን ስራ በማጠናከር የወተት ፍላጎትን በበቂ ሁኔታ ለማሟላት በትኩረት እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል ።
በሁሉም የሌማት ትሩፋት ዘርፎች የክልሉን ህዝብ ተጠቃሚ ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎች አመርቂ መሆናቸውን ገልጸው፤ ከዘርፉ የሚገኘውን የኢኮኖሚ ትሩፋት ለሁሉም ለማዳረስ የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አንስተዋል።

በወላይታ ሶዶ ከተማ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ በሚገኘው ሀገር አቀፍ የእንስሳት አርቢዎች ቀን ዝግጅት ላይ የፌዴራልና የክልል የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ባህርዳር ፤ሚያዝያ 6/2018(ኢዜአ)፡- የአማራ ክልል በቴክኖሎጂ የታገዘ የገቢ አሰባሰብ ስርአትን በመተግበር ረገድ የተገኘው ውጤት ልምድና ተሞክሮ የሚወሰድበት...
Apr 15, 2026
ሮቤ፣ ሚያዝያ 5/2018 (ኢዜአ)፦ የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ዝንባሌ ያላቸው ተማሪዎችን ለተሻለ ውጤት ማብቃት የሚያስችሉ ተግባራትን እያከናወ...
Apr 14, 2026
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025