ወልቂጤ፣ ሐምሌ 16/2017 (ኢዜአ)፡-የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በክትትልና ድጋፍ ተግባሩ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ያጎለበቱ የልማት ሥራዎች እንዲከናወኑ መስራቱን የምክር ቤቱ ዋና አፈ-ጉባኤ ፋጤ ስርሞሎ ገለጹ።
ምክር ቤቱ 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን በወልቂጤ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል ።
በጉባኤ መክፈቻው ላይ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ፋጤ ስርሞሎ እንደገለፁት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ምክር ቤቱ ተከታታይነት ያለው መደበኛ እና ድንገተኛ የክትትል፣ የቁጥጥርና ድጋፍ ሥራዎች ሲያከናውን ቆይቷል።
በዚህም በክልሉ በፖለቲካዊ፣ በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ላይ የተሻለ ለውጥ እንዲመጣ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ሲወጣ መቆየቱን አንስተዋል።
የመንገድ፣ የውሃ፣ የመስኖ እና የጤናን ጨምሮ ሌሎች ማህበራዊ ተቋማት ተግባርን የመከታተል፣ የማረምና የመደገፍ ስራ ማከናወኑንም ተናግረዋል ።
በዓመቱ በክልሉ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን ጀምሮ የመጨረስና የተጓተቱትን አጠናቅቆ ወደ አገልግሎት ከማስገባት አንጻር የተሻለ አፈጻጸምና ልምድ እየታየ መምጣቱን ምክር ቤቱ ማረጋገጡን አንስተዋል።
በዚህም ክልሉ ከተመሰረተ አጭር ጊዜ ቢሆንም ተጓተው የነበሩ ሰፋፊ የልማት ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ወደ ስራ እንዲገቡ በትኩረት መሰራቱን ነው አፈ-ጉባኤዋ የተናገሩት።
በቀጣይም ለሰላም ግንባታ፣ ለልማት እና ለመልካም አስተዳደር ሥራዎች ውጤታማነትና ተፈጻሚነት ምክር ቤቱ የክትትልና የቁጥጥር ሥራዎቹን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
ዛሬ በተጀመረው የዓመቱ ማጠቃለያ መደበኛ ጉባኤም ምክር ቤቱ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ አፌ-ጉባኤዋ ጠቁመዋል።
የምክር ቤቱ መደበኛ ጉባኤ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት እንደሚካሄድ ታውቋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025