የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

የቢሾፍቱ ግብርና ምርምር ማዕከል የእንስሳት ዘርፉን ምርታማነት ለማሳደግ የሚያስችሉ የምርምር ውጤቶችን እያቀረበ ነው

Jul 24, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 17/ 2017 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የቢሾፍቱ ግብርና ምርምር ማዕከል የእንስሳት ዘርፉን ምርታማነት ለማሳደግ የሚያስችሉ የምርምር ውጤቶችን እያሰራጨ መሆኑን ገለፀ።

ማዕከሉ በተለያዩ ሰብልና እንስሳት ላይ ከ70 ዓመታት በላይ ምርምር በማድረግ ዝርያዎችን የማሻሻል ስራ በማከናወን ላይ ይገኛል።


በማዕከሉ የብሄራዊ ዶሮ ምርምር ፕሮግራም አስተባባሪ ሚስባህ አለዊ ለ15 አመት ከተዘጋጀው የዶሮ ምርምር ስትራቴጂ ከተቀዱ ስድስት የምርምር የትኩረት አቅጣጫዎች መካከል ሶስቱ ዝርያ ላይ ያተኮሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ማዕከሉ ለዶሮ አርቢዎችና ለተለያዩ አካላት ስልጠና ከመስጠት ባለፈ የአንድ ቀን ጫጩት አባዝቶ ለአርሶ አደሮች እያሰራጨ ይገኛል ብለዋል።


ከውጭ የሚገቡና ለኮሜርሺያል ዶሮ እርባታ ተስማሚ ዝርያዎችን የመፈተሽ፣ ሀገር በቀል የዶሮ ዝርያን ማሻሻልና ከውጭ የሚገቡ ዝርያዎችን በመጠቀም ለአርሶ አደሮች የሚሆኑ ዝርያዎችን የማልማት ስራ እየሰራ ነው ብለዋል።

የሆሮ ሀገር በቀል ዶሮ ዝርያ በመረጣ የማሻሻል፣ ከውጭ የገቡ ሶስት ዝርያዎችን በማዳቀል ዲዜድ የተሰኘ ዝርያ በምርምር መውጣቱን ገልፀዋል።

በማዕከሉ የብሄራዊ እንስሳት ባዮቴክኖሎጂ ምርምር ፕሮግራም አስተባባሪ ሰኢድ አሊ ማዕከሉ በእንስሳት ዘርፉ ላይ የተለያዩ ምርምሮችን የመስራትና የማስተባበር እንዲሁም የእንስሳት ስነተዋልዶ ባዮቴክኖሎጂ ላይ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።


በዚህም በሰው ሰራሽ ዘዴ ማዳቀል(አርቲፊሻል ኢንሲሜሽን)፣ የኮርማ ፍላጎት ማቀናጀት እንዲሁም ፆታው የተለየ የኮርማ አባላዘር ቴክኖሎጂ የመጠቀም ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በዚህም ላለፉት ሶስት አመታት የወተት መንደሮችን በመመስረት ከ600 በላይ ጥጆች መወለዳቸውን ተናግረዋል።

የፅንስ ዝውውርና በላቦራቶሪ ፅንስ የመፍጠር ስራ ማዕከሉ በእንስሳት ስነተዋልዶ ባዮቴክኖሎጂ ዘርፍ ከሚያከናውናቸው ስራዎች መካከል እንደሚገኙበት አስረድተዋል።

በማዕከሉ የእንስሳት ፕሮግራም አስተባባሪ ካሰች መለሰ እንዳሉት በማዕከሉ ለተሻሻሉ ዝርያዎች የሚመጥኑ የመኖ ልማት ጥናቶች እየተሰሩ ይገኛሉ።


በመኖና ስነ-ምግብ ምርምር የተለያዩ የመኖ ዘሮችን በመፈተሽ አርሶ አደሮች እንዲጠቀሙበት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...

Feb 28, 2025

<p>በዲጂታል አሰራር አማካኝነት የግዥ ስርዓቱን ዓለም አቀፋዊ፣ ግልፅና አሳታፊ ማድረግ ተችሏል</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...

Feb 28, 2025

<p>ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት ነው - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...

Feb 24, 2025

<p>በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል</p>

ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...

Feb 24, 2025