የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በክልሉ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ምቹ ሁኔታን በመፍጠር የውጭ ምንዛሬ አቅምን ለማሳደግ በተከናወነ ሥራ ውጤት ተመዝግቧል

Jul 23, 2025

IDOPRESS

አርባምንጭ ፤ ሐምሌ 15/ 2017 (ኢዜአ)፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ምቹ ሁኔታን በመፍጠር የተኪ ምርቶችን ሚና በማጉላት የውጭ ምንዛሬ አቅምን ለማሳደግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት መመዝገቡን የክልሉ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ።

ኮርፖሬሽኑ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን ለማሳካት ከ40 በላይ አምራች ኢንተርፕራይዞች እና አልሚ ባለሀብቶች የሚሳተፉበት ዐውደ ርዕይና ባዛር በአርባ ምንጭ ከተማ ማዘጋጀቱም ተመላክቷል።

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጥላሁን ብርሃኑ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት ተቋሙ በተሰጠው ተልዕኮ መሠረት በተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ እና በአምራች ኢንተርፕራይዞች ክላስተር ልማት ውጤታማ ስራ እያከናወነ ይገኛል።

ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ምቹ ሁኔታን በመፍጠር የተኪ ምርቶችን ሚና በማጉላት የውጭ ምንዛሬ አቅምን ለማሳደግ በተከናወኑ ሥራዎች ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በአምራች ኢንተርፕራይዞችና አልሚ ባለሀብቶች የጨርቃ ጨርቅ፣ የዘይትና የሞሪንጋ ምርቶችን ወደ ውጭ በመላክ 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ማግኘት ተችሏል ብለዋል።

በአንጻሩም በተኪ ምርት 30 ሚሊዮን ብር የሚሆን የውጭ ምንዛሬን ማዳን መቻሉን ዋና ስራ አስፈጻሚው ገልጸዋል።

በክልሉ ዲላ እና ይርጋጨፈ ሁለት የመካከለኛ ግብርና ኢንዱስትሪ ፓርኮች መኖራቸውን ጠቅሰው የዲላ ግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ በበጀት ዓመቱ 50 ሺህ ሊትር ድፍድፍ የአቮካዶ ዘይት አምርቶ ወደ ውጭ መላኩን ተናግረዋል።

በቡና፣ በወተትና በሌሎች ምርቶች ማቀነባበር ስራ ላይ የሚሰማራው የይርጋጨፌ ግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክ በ2018 ዓ/ም በሙሉ አቅሙ ወደ ሥራ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

በሌላ በኩል በክልሉ በ9 ከተሞች በሚገኙ 17 ክላስተር ማዕከላት 150 ሼዶች መኖራቸውን ጠቅሰው ከነዚህም ውስጥ 126ቱ አምራች ኢንተርፕራይዞች በተለያዩ የሥራ መስኮች ላይ መሰማራታቸውን አስረድተዋል።

ኢንተርፕራይዞቹ በእንጨትና ብረታ ብረት፣ በአግሮ ፕሮሴሲንግ፣ በኬሚካል ውጤቶች፣ በሽመና፣ በቆዳና ሌጦ እንዲሁም በጨርቃ ጨርቅና ሌሎች ስራዎች ላይ በመሰማራት ውጤታማ እየሆኑ ይገኛሉ ብለዋል።

ኮርፖሬሽኑ ከ40 በላይ አምራች ኢንዱስትሪዎች እና አልሚ ባለሀብቶች የሚሳተፉበት ክልል አቀፍ ባዛርና ዐውደ ርዕይን የፊታችን ሐምሌ 17 እና 18 ቀን 2017 ዓ/ም በአርባ ምንጭ ከተማ ለማካሄድ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቀዋል።

ይህም ኢንተርፕራይዞች እና አልሚ ባለሀብቶች ምርቶቻቸውን በማስተዋወቅ የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩ ታስቦ መዘጋጀቱንም አመልክተዋል።

በመርሃ-ግብሩ ላይም በ39 ሚሊዮን ብር የተገነባው የአርባምንጭ ከተማ የአምራች ኢንዱስትሪዎች ሼድ ምረቃ የሚካሄድ ሲሆን የአረንጓዴ አሻራ ልማት እና የኢንዱስትሪ ልማት የምክክር መድረክ አጀንዳዎች እንደሚኖሩም ተጠቁሟል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...

Feb 28, 2025

<p>በዲጂታል አሰራር አማካኝነት የግዥ ስርዓቱን ዓለም አቀፋዊ፣ ግልፅና አሳታፊ ማድረግ ተችሏል</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...

Feb 28, 2025

<p>ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት ነው - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...

Feb 24, 2025

<p>በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል</p>

ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...

Feb 24, 2025