ታርጫ፣ ሐምሌ 15/2017 (ኢዜአ) :- የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ማስፈጸሚያ የሚውል ከ28 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አጽድቋል።
የክልሉ ምክር ቤት በታርጫ ከተማ እያካሄደ በሚገኘው 8ኛው መደበኛ ጉባኤ የሁለተኛ ቀን ውሎው በክልሉ ምክር ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ማስፈጸሚያ የሚውል ከ28 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አፅድቋል።
በክልሉ ምክር ቤት የፋይናንስና በጀት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ የኋላሸት በላይነህ፤ ቋሚ ኮሚቴው ውይይት ካደረገ በኋላ በጀቱ እንዲፀድቅ መወሰኑን ተናግረዋል።
የተያዘውን በጀት ለታለመለት አላማ ማዋል ላይ ሁሉም መዋቅሮች ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባም አሳስበዋል።
በጀቱ በዋናነት ለድህነት ቅነሳ ስራዎች፣ ለዘላቂ ልማት፣ ለስራ እድል ፈጠራና ለሌሎች አገልግሎቶች እንደሚውልም ተናግረዋል።
የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ወሰነች ቶማስ በሰጡት ማብራሪያ የበጀቱ ምንጭ የክልሉ የውስጥ ገቢ፣ ከፌደራል መንግስት የሚሰጥ ድጎማ እና ከሌሎች የገቢ ምንጮች እንደሆነም ገልፀዋል።
በጀቱ አምና ከተበጀተው ጋር ሲነፃፀር 45 በመቶ እድገት እንዳለው አንስተው፣ ከአጠቃላይ በጀቱ ውስጥ 18 ቢሊዮን 257 ሚሊዮን 214 ብር በክልሉ የውስጥ ገቢ የሚሸፈን መሆኑን ተናግረዋል።
ሁሉም ዞኖች የገቢ አሰባሰብ አቅማቸውን ማሳደግ፣ በጀቱን በተገቢው ማስተዳደርና ግልፅነት መፍጠር ላይ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩም ኃላፊዋ አሳስበዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025