የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

ማህበሩ የጥናት እና ምርምር ውጤቶች ተአማኒነት እና የጥራት ደረጃ ማስጠበቅ አለበት- እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር)

Jul 21, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 12/2017(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበር የጥናት እና ምርምር ውጤቶች የተአማኒነት እና የጥራት ደረጃ በልዩ ሁኔታ እንዲያስጠብቅ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) አሳሰቡ።

የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበር የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ አስመልክቶ ያዘጋጀው 22ኛው ዓለም አቀፍ ኮንፍረንስ በአዲስ አበባ ተካሄዷል።

“የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም እና የኢኮኖሚ መረጋጋት በማህበራዊ ደህንነት ውስጥ ያለው አንድምታ” የኮንፍረንሱ መሪ ሀሳብ ነው።

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ እዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበር ከ20 ዓመት በላይ ለፖሊሲ ፋይዳ ያላቸውን ምርምሮች እያደረገ ያለውን አስተዋጽኦ አድንቀዋል።

ማህበሩ ሳይንስን መሰረት ያደረጉ የኢኮኖሚ ምክክሮች ቁልፍ የመወያያ መድረክ ሆኖ እያገለገለ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የተሟላ የስራ ክህሎት እና ስብዕና (ፕሮፌሽናሊዝም)፣ የሳይንሳዊ መረጃ ትንተና ትክክለኛነት እና ኃላፊነት የተሞላበት ተግባቦት የኢትዮጵያን መጻኢ የኢኮኖሚ ሁኔታ የመቅረጽ ሚናቸው ወሳኝ መሆኑን አመልክተዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው ኢትዮጵያ እየተገበረችው ባለው የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙ አማካኝነት ያመጣችውን ለውጥ በንግግራቸው ላይ አንስተዋል።

የዋጋ ንረትን በመቆጣጠር፣ በወጪ ንግድ አፈጻጸም፣ በዘላቂ የእዳ አስተዳደር እና የታክስ ገቢ አሰባሰብ ላይ ከፍተኛ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።

ከማክሮ ኢኮኖሚ ስኬቶቹ ባሻገር ሚኒስትር ዴኤታው ለመንግስት በሚቀርቡ የፖሊሲ አማራጮች ላይ እየታዩ ያሉ ፈተናዎችን አንስተዋል።

የኢኮኖሚ ትንተና እና ተግባቦት ግልጽ፣ ሙያዊ ስነ ምግባርን የጠበቀ እና ኃላፊነት የተሞላበት ሊሆን እንደሚገባው ነው የገለጹት።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዘላቂ የእዳ አስተዳደርን ጨምሮ ጥንቃቄ በሚሹ ጉዳዮች ላይ ግልጽነት የጎደለው መረጃ የማሰራጨትና ወደ አሳሳች ድምዳሜ በሚወስድ መልኩ አግባብ ባልሆነ ሁኔታ ቁጥራዊ መረጃዎችን የመጠቀም አዝማሚያ እየታየ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው አሳሳች እና ግልጽነት የጎደላቸው መረጃዎች ጥርጣሬ በመዝራት የማህበረሰብን እምነት እንደሚሸረሽሩ አመልክተዋል።

አሁን ባለንበት ፈጣን የመረጃ ልውውጥ ዘመን ተአማኒነት እና ግልጽነት ምርጫ አይደለም እጅግ አስፈላጊ ነገር ነው ብለዋል።

በዚህ ረገድም የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበር ትንታኔዎች በከፍተኛ ደረጃ መመኛን ያሟሉ፣ ስሜት ቀስቃሽነትን ያስወገዱ እና ከፖለቲካዊ ብያኔዎች የጸዱ እንዲሆኑ በልዩ ኃላፊነት መስራት እንዳለበት አሳስበዋል።

ሚኒስትር ዴኤታው የገንዘብ ሚኒስቴር ከማህበሩ እና ከሌሎች ተቋማት ጋር መረጃ እና በተአማኒና እውነተኛ መረጃ የተደገፈ የፖሊሲ ልማት እንዲጠናከር በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

በኮንፍረንሱ ላይ የኢኮኖሚ ባለሙያዎች፣ ምሁራን፣ ፖሊሲ አውጪዎች እና ተመራማሪዎች የተገኙ ሲሆን በቁልፍ የኢኮኖሚ ጉዳዮች እና የፖሊሲ አቅጣጫዎች ላይ መወያየታቸውን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...

Feb 28, 2025

<p>በዲጂታል አሰራር አማካኝነት የግዥ ስርዓቱን ዓለም አቀፋዊ፣ ግልፅና አሳታፊ ማድረግ ተችሏል</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...

Feb 28, 2025

<p>ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት ነው - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...

Feb 24, 2025

<p>በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል</p>

ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...

Feb 24, 2025