ሮቤ ፤ ሐምሌ 2/2017(ኢዜአ)፦በሮቤ ከተማ የግብር አሰባሰብ ስርዓትን ቀልጣፋና ፍትሃዊ በማድረግ ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ ለመሰብሰብ የሚያስችሉ ስራዎች እንደሚጠናከሩ የከተማው ገቢዎች ጽህፈት ቤት ገለጸ።
የሮቤ ከተማና የዞኑ ገቢዎች ጽህፈት ቤት የደረጃ "ሐ" ግብር ከፋዮች የንቅናቄ መድረክ አካሄደዋል።
የሮቤ ከተማ ገቢዎች ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ መሰለች በዬቻ እንዳሉት በከተማው የግብር አሰባሰብ ስርዓትን በማዘመን ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ ለመሰብሰብ የሚያስችሉ ተግባራት ተጠናክረው ቀጥለዋል።
በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከተለያዩ አርዕስቶች ከ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን አመልክተዋል።
በዘንድሮ የበጀት ዓመትም የገቢ አሰባሰብ ሂደትን በማዘመንና አዳዲስ የገቢ አማራጮችን በመፈተሽ ከ2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ የደረጃ ´´ሐ´´ የግብር ከፋዮችን ያሳተፈ የንቅናቄ መድረክ መጀመሩን ተናግረዋል።
በዚህም በከተማዋ ከ8 ሺህ የሚበልጡ የደረጃ ´´ሐ´´ የግብር ከፋዮችን በማሳተፍ ትናንት በተካሄደ የግብር ንቅናቄ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን አመልክተዋል።
በሌላ በኩል በባሌ ዞን በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከ2 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን የዞኑ ገቢዎች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታጁዲን ሀሱ ተናግረዋል።
በአዲሱ የበጀት ዓመት የግብር አሰባሰብ ሂደትን ቀልጣፋና ፍትሃዊ በማድረግ ከ3 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለመሰብሰብ ወደ ሥራ መገባቱን አስረድተዋል።
በተለይ የግብር ስወራን በመቆጣጠር፣ ህገ ወጥ ነጋዴዎችን ወደ ግብር መረቡ ማስገባት በአዲሱ በጀት ዓመት ትኩረት ከሚሰጣቸው ስራዎች መካከል ዋናኞቹ መሆናቸውን አቶ ታጁዲን ጠቅሰዋል።
በሮቤ ከተማ የደረጃ 'ሐ' የግብር ከፋዮች መካከል አቶ መሐመድ ከድር በሰጡት አስተያየት ግብርን በአግባቡ መክፈል ለአገር ልማት ያለው አስተዋጽኦ ትልቅ በመሆኑ የሚጠበቅባቸውን ግብር በወቅቱ እንደሚከፍሉ ተናግረዋል።
አቶ አህመድ ማህሙድ በበኩላቸው የግብር አሰባሰብ ሂደቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ በመምጣቱ ግብርን በወቅቱ ለመክፈል እንዳነሳሳቸው ገልጸዋል።
በሮቤ ከተማ አስተዳደር እና የባሌ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች 20 ሺህ የሚሆኑ የግብር ከፋዮች የሚገኙ ሲሆን ከነዚህ መካከል 88 ነጥብ 7 በመቶ የሚሆኑት የደረጃ ´´ሐ´´ የግብር ከፋዮች መሆናቸው ተጠቁሟል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025