አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29/2017(ኢዜአ)፦ ወጣቶች የትኛውንም አስቸጋሪ ሁኔታ ወደ መልካም አጋጣሚ በመቀየር በሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት ላይ የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስገነዘቡ።
የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር 8ኛ መደበኛ ጉባኤ በአዲስ አበባ ዓድዋ ድል መታሰቢያ ተካሒዷል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በጉባኤው ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት መንግስት የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።
ለአብነትም ከተማ አስተዳደሩ በአመራር ዘርፍ የወጣቶችን ተሳትፎ ለማረጋገጥ አካታች የፖለቲካ ስርዓትን ተግባራዊ ማድረጉን አንስተዋል።
እንዲሁም የወጣቶች ሰብዕና መገንቢያ ማዕከላት፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎችን ጨምሮ የስራ ዕድል ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ሁኔታ ማመቻቸት የከተማ አስተዳደሩ የትኩረት አቅጣጫ ነው ብለዋል።
የብልፅግና ጉዞን ከዳር ለማድረስ የሚደረገውን ጥረት ለመምራት ወጣቶች በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባም ነው ከንቲባዋ ያስገነዘቡት።
የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር በስነ-ምግባር የታነፁ በእውቀትና በአቅም የዳበሩ ወጣቶችን ማፍራት ላይ እያከናወነ ያለውን ተግባር አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም ገልጸዋል።
ወጣቶች የትኛውንም አስቸጋሪ ሁኔታ ወደ መልካም አጋጣሚ በመቀየር በሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት ላይ የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ በላይ ደጀን በበኩላቸው የከተማዋ ወጣቶች በሰላም ግንባታ፣ በአረንጓዴ አሻራና መሰል የልማት ስራዎች ላይ የሚያደርጉት ተሳትፎ ላቅ ያለ መሆኑን ገልጸዋል።
በተጨማሪም በበጎ ፍቃድ አገልግሎት በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ሀገራዊ ሀላፊነታቸውን እየተወጡ ስለመሆኑም አንስተዋል።
ከተማ አስተዳደሩ የወጣቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ባከናወናቸው ተግባራት አዲስ አበባን የሰላም፣ የፍቅርና የአብሮነት ከተማ እንድትሆን ማድረግ ችሏል ብለዋል።
የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር ሰብሳቢ ገዛኸኝ ገብረማሪያም፤ ማህበሩ ወጣቶች በሀገር ሁለንተናዊ ዕድገትና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እየተወጣ መሆኑን ገልጿል።
በመንግሥት የሚከናወኑ የልማትና መሰል ተግባራትን በማጠናከር ሒደት ወጣቱ በባለቤትነት እንዲሳተፍ የተለያዩ መርሃ-ግብሮችን በማዘጋጀት የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ መሆኑንም አብራርቷል።
በተለይም ወጣቱ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ በስራ ዕድል እና በኮሪደር ልማት ስራ እና በሌሎች ዘርፎች ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆን ማህበሩ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ጠቁሟል።
በዚህም መንግስት የወጣቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የፈጠረውን ምህዳር ለመጠቀም አስቻይ ሁኔታ ፈጥሯል ብሏል።
በጉባኤው ላይ ማህበሩን በተለያየ መልኩ ለሚያግዙ ተቋማትና ማህበራት እውቅና የመስጠት መርሃ-ግብርም ተካሒዷል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025