አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29/2017(ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለመንገድ ግንባታ የሰጠውን ትኩረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ 21 ፕሮጀክቶችን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።
በምረቃ መርሃ ግብሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ቡዜና አልከድር እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ የሀይማኖት አባቶች አባገዳዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በወቅቱ እንደገለጹት፤ ከተማ አስተዳደሩ ከተማዋን ለማዘመን ከኮሪደር ልማት ስራዎች ባሻገር የመንገድ መሰረተ ልማት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በልዩ ትኩረት በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል።
በበጀት አመቱ ከተማ አስተዳደሩ የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ በርካታ ፕሮጀክቶች ማከናወኑን ገልጸዋል።
በዛሬው እለት 31 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያላቸዉ 13 የመንገድ ፕሮጀክቶችንና 8 ድልድዮችን አጠቃላይ 21 ፕሮጀክቶችን መርቀው ለአገልግሎት ክፍት መደረጋቸውን ተናግረዋል።
ፕሮጀክቶቹ በመንግስትና በህብረተሰብ ተሳትፎ የተከናወኑ መሆናቸውን ያመላከቱት ከንቲባዋ፤ በዋናነት የህብረተሰቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ናቸው ብለዋል።
በቀጣይ ለእድገት ዋና መሰረት የሆነውን የመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታ ከተማ አስተዳደሩ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሞዲን ረሻድ(ኢ/ር) በበኩላቸው፤ ከተማ አስተዳደሩ ባለፉት ዓመታት ባከናወናቸው የመሰረተ ልማት ግንባታ በርካታ መንገዶች ተገንብተው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል ብለዋል።
በ2017 በጀት ዓመት የአስፓልት የኮብልስቶን ንጣፍ ጠጠር መንገድ የእግረኛ መንገድ የድጋፍ ግንብ እና የማፋሰሻ ቦዮች ግንባታዎችን ጨምሮ 371 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የመንገድ መሰረተ ልማት መገንባቱን ተናግረዋል።
በዚህ ምረቃ ግዙፍ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች የሆኑት የቃሊቲ ቱሉ ዲምቱ እና የቃሊቲ ቅሊንጦ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች እንደሚገኙበትም ገልጸዋል።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025