አዲስ አበባ፤ ሰኔ 26/2017(ኢዜአ)፦ በግብርናው ዘርፍ ሜካናይዜሽን የሚያስፋፉ በሺህ የሚቆጠሩ ትራክተሮችን በማስገባትና የመስኖ ልማትን በማስፋፋት ምርታማነትን ማሳደግ መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አስታወቁ፡፡
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 42ኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግብርናን ለማሳደግ የተከናወኑ ተግባራትን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ ኢትዮጵያ ሰፊ ሊታረስ የሚችል መሬት ካላቸው ሀገራት መካከል አንዷ መሆኗን አንስተዋል።
ለግብርናው ዘርፍ በተሰጠው ትኩረት አምና 26 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ታርሶ አንድ ነጥብ ሁለት ቢሊዮን ኩንታል ምርት ተገኝቶ እንደነበር አስታውሰዋል።
ዘንድሮ ለዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት አጠቃላይ ሰላሳ ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ሄክታር መሬት ታርሶ አንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ኩንታል ምርት መሰብሰቡን ገልጸዋል።
በዚህም ዘንድሮ ከአምናው አምስት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ሄክታር መሬት ጭማሪ በማረስ ሶስት መቶ ሚሊዮን ኩንታል ምርት ማግኘት ማቻሉን ነው ያብራሩት።
ግብርናውን ሜካናይዝድ ለማድረግና ምርትን ለማሳደግ በሺዎች የሚቆጠሩ ትራክተሮችና ፓምፖች ጥቅም ላይ መዋላቸውንና የግብርና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችም በእያንዳንዱ አርሶ አደር ማሳ ላይ ቀን ከሌት እየተጉ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በግብርናው ዘርፍ አዳዲስ የስራ ልምምድ መኖሩን ያወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሞቃታማ አካባቢዎች ማታ ጭምር እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡
ኖራን በማምረት ከ50ሺህ ሄክታር በላይ አሲዳማ መሬት ታክሞ ወደ እርሻ መግባቱን ገልፀው መሬትን ደጋግሞ የማረስና በአመት ሁለቴ ሶስቴ የማምረት ልምምድ ማደጉን በተለይ የበጋ መስኖ መጀመሩ ከፍተኛ እመርታ አምጥቷል ብለዋል፡፡
በሌማት ትሩፋት በዶሮ ልማት፣ የእንቁላልና የወተት ምርት ያደገበት፣ በሰው ሰራሽ ማዳቀል ዘዴ ምርታማነትን በመጨመር የወተት ፍጆታ በግለሰብ 66 ሊትር የነበረው ወደ 80 ሊትር ማደጉንም ተናግረዋል፡፡
በማር እና በአሳ የታዩ ከፍተኛ ለውጦች እንደ መልካም ጅማሮ የሚወሰዱና ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን መተካት መቻሉን በመጥቀስ ይህ ተጠናክሮ ሲቀጠል በብዙ ዘርፍ ውጤታማ መሆን እንደሚቻል አውስተዋል፡፡
በቡና፣ በሻይና በሩዝ ልማት ላይም ለውጥ መኖሩን ጠቅሰው ግብርናው ትኩረት የተሰጠውና ትልቅ ውጤት ያመጣ እንዲሁም ለአጠቃላይ እድገታችን ትልቅ ድርሻ ያለው ነው ብለዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025