የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በአፍሪካ ሲቪል ሰርቪስ አገልግሎት መዋቅራዊ  ለውጥ ለማምጣት አሰራርን በቴክኖሎጂ መደገፍ ሊጠናከር ይገባል

Jun 23, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 15/2017(ኢዜአ)፦በአፍሪካ ሲቪል ሰርቪስ አገልግሎት መዋቅራዊ ለውጥ ለማምጣት አሰራርን በቴክኖሎጂ መደገፍ እንደሚያስፈልግ ተመላከተ።

በአዲስ አበባ አፍሪካ ህብረት አዳራሽ ትላንት መካሄድ የጀመረው 10ኛው የአፍሪካ የፐብሊክ ሰርቪስ ቀን በተለያዩ መርሃ ግብሮች ዛሬም ቀጥሏል።


በአህጉሪቱ የፐብሊክ ሰርቪስ አካታችነት፣ አሰራርና ህጋዊ ማዕቀፎችን ላይ በተደረገ የፓናል ውይይት አገራት ልምዳቸውን አጋርተዋል።

በፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የመንግስት ሰራተኞች ስራ ስምሪት መሪ ስራ አስፈጻሚ ጌታቸው ዋጋው(ዶ/ር) ኢትዮጵያ ዲጂታላይዜሽን ከማስፋፋት አኳያ ያላትን ልምድና የሚወሰዱ ተሞክሮዎችን አቅርበዋል።

በወቅቱ አሰራርን ዲጂታላይዝ በማድረግ ለዜጎች ወቅቱን የጠበቀና በቂ መረጃ ማቅረብ ተጠያቂነትን ለማስፈን አጋዥ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያም በዲጂታል አሰራር የታገዘ የሲቪል ሰርቪሰ አሰራር ለማጠናከር በርካታ ተግባራትን እያከናወነች እንደምትገኝ ገልጸዋል።

የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 የተለያዩ ተቋማት አገልግሎታቸውን በኦንላይን የሚሰጡበት አሰራር እየተስፋፋ ሲሆን ለአብነትም መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን አንስተዋል።

በርካታ የአፍሪካ አገራት በዲጂታል አሰራር የተደገፈ ሲቪል ሰርቪስ ለመገንባት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።

በአፍሪካ የተሻለ የሲቪል ሰርቪስ አገልግሎት ስርዓት ለመገንባት በጋራ የሚሰሩትን ተግባራት ማጠናከር እንደሚገባም አስገንዝበዋል።


የኬንያ ሲቪል ሰርቪስ ተቋም የሆነው "ኬንያ ስኩል ኦፍ ጋቨርንመንት" ዋና ዳሬክተር ተባባሪ ፕሮፌሰር ሉዲኪ ቹዌያ በበኩላቸው ኬንያ አካታች አገልግሎት ለመስጠት የተከተለችውን አሰራር አብራርተዋል።

በአፍሪካ አገራት በሲቪል ሰርቪስ አገልግሎት የህግ ማዕቀፍ አሰራሮች ቢኖሩም በተግባር አካታችና ፈጣን አገልግሎት ከመስጠት አንጻር ክፍተቶች እንዳሉ አንስተዋል።

አካታችና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት መዋቅራዊና የአስተሳሰብ ለውጥ እንደሚያስፈልግ አመላክተዋል።

በአህጉር ደረጃ የሚካሄዱ ውይይቶችና የልምድ ልውውጦች ዘመናዊ ሲቪል ሰርቪስ በመገንባት ዜጎችን በእኩልነት የሚያገለግል አሰራር ለመዘርጋት ያግዛል ብለዋል።


በተባበሩት መንግስታት የምጣኔ ሃብትና ማህበራዊ ጉዳይ ክፍል የፕሮግራም ማናጅመንት እና አቅም ግንባታ ቡድን መሪ አድሪያና አልበርቲ(ዶ/ር) ለአገልግሎት አሰጣጥ መሻሻል መሰረታዊ ጉዳዮችን አንስተዋል።

ተራማጅ አስተሳሰብ፣ፈጠራ፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራር፣ ዜጎችን ያሳተፈና ተጠያቂነትን የሚያሰፍን የአስተሳሰብ ለውጥ እንደሚያስፈልግ ዘርዝረዋል።

10ኛው የአፍሪካ የሲቪል ሰርቪስ ቀን በአፍሪካ ቀልጣፋ፣ ንቁና ጽኑ የመንግስት ተቋማትን በመገንባትና የአገልግሎት አሰጣጥ ችግርን በመፍታት ፍትሃዊ አስተዳደር መገንባት ላይ ትኩረት አድርጎ እየተካሄደ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...

Feb 28, 2025

<p>በዲጂታል አሰራር አማካኝነት የግዥ ስርዓቱን ዓለም አቀፋዊ፣ ግልፅና አሳታፊ ማድረግ ተችሏል</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...

Feb 28, 2025

<p>ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት ነው - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...

Feb 24, 2025

<p>በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል</p>

ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...

Feb 24, 2025