አዲስ አበባ፤ሰኔ 14/2017 (ኢዜአ)፦መንግስት በየአካባቢው ያሉ ፀጋዎችን በመለየት የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ እያከናወናቸው የሚገኙ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ገለፁ።
ከለውጡ በኃላ በቱሪዝሙ ዘርፍ ከተከናወኑ ስራዎች መካከል አንዱ የሆነው የቤኑና መንደር በተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ተጎብኝቷል።
የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ሰሞኑን በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር ውይይት ማካሄዳቸው የሚታወቅ ነው።ከውይይቱ በኋላ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።
የዶንጋ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት አመራር አቶ ለገሰ ለመንጎ፥ ከጎበኟቸው የልማት ሥራዎች መካከል የቤኑና መንደር ተአምር እንደሆነባቸው አንስተዋል።
የጎጎት ለጉራጌ አንድነትና ፍትህ ፓርቲ አመራር የሆኑት ወይዘሮ ሂንዲያ ሻፊ በበኩላቸው በተመለከቱት የልማት ሥራ መደነቃቸውን ነው የገለፁት።
የዓረና ትግራይ ፓርቲ አመራር አቶ ሀፍተይ ገብረሩፋኤል በሰጡት አስተያየት የቱሪዝም ዘርፉን ለማነቃቃት የተከናወኑት ተግባራት መልካም መሆናቸውን የተገነዘብንበት ጉብኝት ነው ብለዋል።
ቱሪዝም ከሰላም ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳለው በመጥቀስ፥ በተለያዩ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ አካላት ችግራቸውን በውይይት በመፍታት ለዘርፉ እድገት አበርክቶ ሊያደርጉ እንደሚገባም ነው ያነሱት።
የተለያዩ የፖለቲካ አመለካከቶች ቢኖሩም በሀገር ጉዳይ ላይ በትብብር መስራት ተገቢ ነው ያሉት የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮቹ ለዚህም በቀጣይ የእኛስ አበርክቶ ምን ሊሆን ይገባል የሚለውን የቤት ስራ የሰጠ ጉብኝት ነው ብለዋል።
እንዲህ አይነት የሀገርን እድገት የሚያልቁ ተግባራትን ለመከወን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያሳዩት ቁርጠኝነትም የሚያስመሰግናቸው መሆኑን አንስተዋል።
በእድገት ጉዞ ውስጥ አሻራቸውን ያሳረፉ ባለሙያዎችም ሀገራቸውን ለማልማት ላከናወኑት ስራ አድናቆት አለን ነው ያሉት።
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025