ሆሳዕና ፤ ሰኔ 13/2017(ኢዜአ) አዳዲስ የፈጠራና ቴክኖሎጂ ውጤቶች ለሀገር እድገት እና የህዝብን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ረገድ የላቀ ሚና እንዳላቸው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አንተነህ ፈቃዱ ገለጹ።
ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልልን "የሳይንስ ኢኖቬሽንና የቴክኖሎጂ ማዕከል እናድርግ" በሚል መሪ ሃሳብ በወልቂጤ ከተማ ለሁለት ቀናት የተካሄደው የሳይንስና ፈጠራ ስራዎች አውደ ርዕይ እና ውድድር ተጠናቋል፡፡
በማጠቃለያ መርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አንተነህ ፈቃዱ፤ አዳዲስ የፈጠራና ቴክኖሎጂ ውጤቶች ለሀገር እድገትና የህዝብን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ረገድ ሚናቸው የላቀ ነው ብለዋል።
በመሆኑም የማህበረሰብ ችግሮችን መሰረት ያደረጉ የሳይንስና የፈጠራ ውጤቶችን ስኬታማ ለማድረግ ከትምህርት ተቋማትና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
በእውቀትና በክህሎት ላይ የተመሰረተ አሰራርን በማጠናከር የክልሉን ብሎም የሀገርን እድገት እውን ለማድረግ መትጋት ይኖርብናልም ብለዋል።
የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ ሰላሙ አማዶ፤ የፈጠራና የቴክኖሎጂ ውጤቶች ከሀገርም የተሻገረ ፋይዳ እንዲኖራቸው ማዳበርና ማሳደግ ያስፈልጋል ብለዋል።
የክልሉ ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ኢሳ ኢንተርፕራይዞች አዳዲስ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ውጤቶችን በመቅዳትና ለማህበረሰቡ በማሸጋገር ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ትልቁን ድርሻ እንደሚወስዱ ተናግረዋል፡፡
በኤግዚቢሽኑ የፈጠራ ስራቸውን ካቀረቡ ተማሪዎች መካከል በወልቂጤ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ11ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው እሱባለው ተክለወልድ የግብርና ቴክኖሎጂን ለማዘመን የሚያግዝ የፈጠራ ስራ ይዞ መቅረቡን ተናግሯል።
የፈጠራ ስራው የገጠሩን ማህበረሰብ ግብርናን በማዘመን ከድህረ ምርት እስከ ምርት ሂደት በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የታገዘ ክትትል ለማድረግና ምርታማነትን ለመጨመር የሚያስችል መሆኑን ነው የገለጸው።
በመርሐ ግብሩ ላይ የፈጠራ ባለቤቶች፣ የክልል፣ የዞንና የልዩ ወረዳ አመራሮችና የተለያዩ ባለድርሻ አካላትም ተሳትፈዋል፡፡
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...
Feb 28, 2025
አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...
Feb 24, 2025
ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...
Feb 24, 2025