የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በክልሉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በሁሉም መስክ ህዝብን ተጠቃሚ ያደረጉ ልማቶች ተከናውነዋል

Apr 22, 2025

IDOPRESS

ሐረር፤ ሚያዝያ 14/2017(ኢዜአ)፡- በሐረሪ ክልል ባለፉት ዘጠኝ ወራት በሁሉም መስክ የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ የልማት ስራዎች መከናወናቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦርዲን በድሪ ገለፁ።

የክልሉ የአስፈፃሚ እና የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ዘርፎች የበጀት ዓመቱ የዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃፀም እየተገመገመ ነው።


የግምገማውን መድረክ እየመሩ የሚገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ እንዳሉት፤ በክልሉ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የገጠርና የከተማ ነዋሪዎችን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ልማቶች ተከናውነዋል።

በማህበራዊ፣ በምጣኔ ሃብት እና በመልካም አስተዳደር መስኮች የተከናወኑ ስራዎች የክልሉን ታሪካዊ፣ ተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ ሃብቶች በላቀ ደረጃ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ማስቻሉን በመጥቀስ።

እነዚህን ውጤቶች ይበልጥ ለማስቀጠል የግምገማው መድረክ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው፤ በተለይም በግምገማው የተንጠባጠቡ ስራዎችና ክፍተቶች ተለይተው እስከ ሰኔ 30 ድረስ በተቀናጀ መንገድ ለማጠናቀቅ መደላድል ይፈጠራል ብለዋል።


በግምግማው መድረክ ላይ የክልሉ የፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኢብሳ ኢብራሂም የዘጠኝ ወራት የካፒታል ፕሮጀክቶች የስራ አፈፃፀም ሪፖርት በማቅረብ ላይ ናቸው።

ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ግምገማ ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና የየወረዳ አመራሮችና ባለሙያዎች ተሳታፊ ናቸው።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

<p>የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...

Feb 28, 2025

<p>በዲጂታል አሰራር አማካኝነት የግዥ ስርዓቱን ዓለም አቀፋዊ፣ ግልፅና አሳታፊ ማድረግ ተችሏል</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...

Feb 28, 2025

<p>ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት ነው - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ</p>

አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...

Feb 24, 2025

<p>በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል</p>

ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...

Feb 24, 2025