የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ

በጌዴኦ ዞን ባለ ልዩ ጣዕም ቡና ልማትን ለማስፋፋት እየተሰራ ነው

Jan 18, 2025

IDOPRESS

ሀዋሳ፤ ጥር 9/2017(ኢዜአ)፡- በጌዴኦ ዞን በተያዘው ዓመት ባለ ልዩ ጣዕም ቡና ልማትን ለማስፋፋት እየተሰራ መሆኑን የዞኑ ቡናና ቅመማቅመም ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

በዞኑ ለተያዘው ዓመት ተከላ የሚሆን ከ8 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ የቡና ዘር መዘጋጀቱ ተመላክቷል።

የጽህፈት ቤቱ ሀላፊ አቶ ኤርሚያስ ቸካ ለኢዜአ እንደገለጹት የባለ ልዩ ጣዕም የቡና ዘር የተዘጋጀው በዞኑ ይርጋጨፌና ገደብ ወረዳዎች በሚገኙ ሁለት ማህበራት በኩል ነው።

አምና ለጌዴኦ ዞን ብቻ የዋለ 3ሺህ 400 ኪሎ ግራም ዘር ተዘጋጅቶ በዞኑ ለሚገኙ ቡና አምራች ወረዳዎች መሰራጨቱን አስታውሰዋል።

ዘንድሮም ባለ ልዩ ጣዕም ቡና ልማትን ለማስፋፋት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፣ በዚህም በተመረጡ ሞዴል አርሶ አደሮች 8ሺህ 200 ኪሎ ግራም የባለ ልዩ ጣዕም ቡና ዘር መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

ዘንድሮ የተዘጋጀው የቡና ዘር ከዞኑ ባለፈ ለሌሎች ዞኖች እንደሚሰራጭ ተናግረዋል።

በዞኑ የይርጋጨፌ ባለ ልዩ ጣዕም ቡና ጣዕሙን ይዞ እንዲቀጥል ለማድረግ ከእንክብካቤ ጀምሮ ያረጀ ቡናን በመጎንደል የማደስ፣ ነቅሎ የመተካትና በተጨማሪ አዲስ ማሳ የመትከል ሥራ እየተሰራ መሆኑንም አቶ ኤርሚያስ አስረድተዋል።

በቡና ልማት ሞዴል የሆኑትና በይርጋጨፌ ወረዳ ቆንጋ ቀበሌ የሚኖሩት አርሶ አደር ዳንኤል ደምሴ እንዳሉት ባላቸው 2 ነጥብ 8 ሄክታር የቡና ማሳ ላይ የይርጋ ጨፌንባለ ልዩ ጣዕም ቡና ያመርታሉ።

ለቡና ማሳቸው በሚያደርጉት እንክብካቤ የሚያገኙት የምርት መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ተናግረዋል።

ቀደም ባሉት ዓመታት የቡና ዘር በተናጠል ይዘጋጅ እንደነበር አስታውሰው፣ በተያዘው ዓመት በኩታ ገጠም በማህበር ተደራጅተው ያዘጋጁትን ዘር ለዞኑ ማስረከባቸውን ገልጸዋል።

ሌላው ሞዴል አርሶ አደር ሙሉጌታ ከበደ እንዳሉት ያላቸውን 6 ነጥብ 8 ሄክታር የቡና ማሳ በአግባቡ በመንከባከብ የሚያገኙትን ምርትና ገቢ እያደገ መጥቷል።

በየዓመቱ በኩታ ገጠም ማሳቸው ያረጀውን ቡና በመጎንደል፣ የማደስና በአዲስ የመተካት ስራ በመስራታቸው ምርታማነታቸው መጨመሩን ገልጸዋል።

አምና ከቡና ንግድ 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ገቢ አግኝተው እንደነበር ያስታወሱት አርሶ አደሩ፣ ዘንደሮ እስከ ሦስት ሚሊዮን ብር አገኛለሁ ብለው እንደሚጠብቁ ገልጸዋል።

ለዘር አቅርቦት ማህበሩ የሚያስገቡት 6 ኩንታል ዘር ማዘጋጀታቸውንም ተናግረዋል።

በይርጋጨፌ ወረዳ ቡናና ቅመማቅመም ጽህፈት ቤት የቡና አግሮኖሚስትና ኤክስቴንሽን ኮሙኒኬሽን ባለሙያ አቶ ጋሻው ስሜ እንዳሉት፣ በወረዳው ከሚገኙ 26 ቀበሌዎች 24ቱ ባለ ልዩ ጣዕም ቡና አምራች ናቸው።

በእነዚህ ቀበሌዎች በአጠቃላይ 20ሺህ 980 ሄክታር መሬት በቡና መሸፈኑን ገልጸው፣ በሄክታር በአማካይ 10 ነጥብ 8 ኩንታል ምርት ይገኛል ብለዋል።

በወረዳው 70 ሞዴል አርሶ አደሮችን ያቀፈ የዘር አቅርቦት ማህበር እንደሚገኝና 3ሺህ 500 ኪሎ ግራም ዘር መዘጋጀቱን አስረድተዋል።

በጌዴኦ ዞን በ135 ሺህ አባወራና እማወራ አርሶ አደሮች 76 ሺህ ሄክታር መሬት በቡና መሸፈኑን ከዞኑ ቡናና ቅመማቅመም ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው - ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ የስንዴ ልማት ስራዎችን ለማስፋት መንግስት በትኩረት እየሰራ ነው ሲሉ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገ...

Feb 28, 2025

በዲጂታል አሰራር አማካኝነት የግዥ ስርዓቱን ዓለም አቀፋዊ፣ ግልፅና አሳታፊ ማድረግ ተችሏል

አዲስ አበባ፤ የካቲት 20/2017(ኢዜአ)፦ባለፉት ስድስት ዓመታት የፋይናንስ ዘርፉንና የመንግስት አገልግሎቶችን ወደ ዲጂታል አሰራር በመቀየር የግዥ ስርዓቱን ዓ...

Feb 28, 2025

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት ነው - ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ

አዲስ አበባ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የቀጣናውን ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ፕሮጀክት መሆኑን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳን...

Feb 24, 2025

በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብተዋል

ጋምቤላ፤ የካቲት 15/2017(ኢዜአ)፡- በጋምቤላ ክልል በቆላማ አካባቢዎች ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የዜጎችን ተጠቃሚነት እውን ያደረጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች ተገንብ...

Feb 24, 2025