የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ቀልጣፋ አገልግሎት እንድናገኝ አስችሎናል-ተገልጋዮች

May 6, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አምቦ ፣ሚያዚያ 26/2018 (ኢዜአ)፦መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መጀመሩ እንግልትን በማስቀረት ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለማግኘት ምቹ ሁኔታ ፈጥሮልናል ሲሉ የአምቦ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።

በማዕከሉ የመኖሪያ ቤት ግንባታ ፍቃድ ለማውጣት የመጡት አቶ ፍቃዱ ባይሳ ለኢዜአ እንዳሉት ፤ አገልግሎቱ በቴክኖሎጂ የተደገፈና ከወረቀት ንክኪ የፀዳ በመሆኑ ጉዳያቸውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅ ችለዋል።


በተለይ ሁሉንም ዓይነት አገልግሎት በአንድ ስፍራ በተሟላና ቀልጣፋ በሆነ አግባብ ማግኘት መቻላቸው ከዚህ በፊት የነበረውን አላስፈለጊ ወጪና እንግልት እንዳስቀረላቸው ነው የሚናገሩት።

የመሬት ይዞታ ባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ለሙውሰድ ወደ ማእከሉ መምጣታቸውን የሚናገሩት ወይዘሮ ብርቄ ጣሶ ፤በማዕከሉ የሚፈልጉትን አገልግሎት በፍጥነት ለማግኘት መቻላቸውን ተናግረዋል።


በተለይም በአንድ ቦታ የተሟላና ፈጣን አገልግሎት ማግኘት መቻሉ ከዚህ በፊት ይገጥሙ የነበሩ ችግሮችን እንዳስቀረ ነው ያነሱት።

ጉዳያቸውን በአጠረ ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ቀልጣፋ አገልግሎት ማግኘት መቻላቸውን የገለጹት ደግሞ የመኖሪያ ቤት የሊዝ ውል ስምምነት ለመፈጸም ወደ ማእከሉ የመጡት አቶ ጂረኛ ተረፈ ናቸው።


አገልግሎት አሰጣጡም ቀልጣፋ፣ምቹ እና ድካምን ያስቀረ ሆኖ እንዳገኙትም ነው የተናገሩት።

የአምቦ ከተማ አስተዳደር መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አራርሳ ከበደ በበኩላቸው፤ ማዕከሉ በአንድ ቦታ 107 አገልግሎቶችን መስጠቱ ማሕበረሰቡ ይደርስበት የነበረውን እንግልት ለማስቀረት አስችሏል ብለዋል።


በተለይም በዘርፉ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ይነሱ የነበሩ በርካታ ቅሬታዎችን ለመፍታት እንዳስቻለም ነው የተናገሩት።

በማዕከሉ የአገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋት፣ ግልፅና ቀልጣፋ ለማድረግና የተገልጋዮችን እርካታን በተሻለ መልኩ ለመጨመር በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በማዕከሉ 18 የከተማው ሴክተር ጽህፈት ቤቶች 107 አገልግሎቶችን በተሟላ መልኩ እየሰጡ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ቱሪዝም የሀገራዊ ዕድገታችንን የወደፊት አቅጣጫ እየቀረጸ ያለ ዘርፍ መሆኑን እያስመሰከረ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 

‎አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 11/2018 (ኢዜአ)፡- ቱሪዝም የኢኮኖሚያችን አንዱ ምሰሶ እንደመሆኑ የሀገራዊ ዕድገታችንን የወደፊት አቅጣጫ እየቀረጸ ያለ ዘርፍ መሆኑ...

Apr 20, 2026

የኮደርስ ስልጠና ቀልጣፋና ዘመናዊ የሕዝብ አገልግሎት መስጠት አስችሏል

ጅማ፤ ሚያዝያ 6/2018(ኢዜአ)፡- በጅማ የኮደርስ ስልጠና የወሰዱ የመንግሥት ሠራተኞች ቀልጣፋና ዘመናዊ የሕዝብ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ እያገዛቸው መሆኑን...

Apr 14, 2026

በምዕራብ ሸዋ ዞን የፍራፍሬ ልማትን የማስፋፋት ስራ በትኩረት እየተከናወነ ነው

አምቦ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን የፍራፍሬ ልማትን የማስፋፋት ስራ በትኩረት እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር ገለጸ።...

Mar 27, 2026

ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የደረሰው የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሂደት

በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ጥያቄ ያቀረበችው እ.አ.አ 2003 ነበር። ኢትዮጵያ በወቅቱ ጥያቄውን ካቀረበች በ...

Mar 27, 2026