🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 23/2018 (ኢዜአ)፦ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዘው የተቀናጀ የሚዲያ ሬጉላቶሪ እና የአስተዳደር ስርዓት ሐሰተኛ መረጃና የጥላቻ ንግግርን ለመከላከልና መቆጣጠር ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሃይማኖት ዘለቀ ገለጹ።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ጋር በመተባበር ያለማውን የተቀናጀ የሚዲያ ሬጉላቶሪ እና አስተዳደር ስርዓት ቴክኖሎጂ የማስጀመሪያ መርሐ ግብር በመካሄድ ላይ ነው።

በመርሐ ግብሩ ላይ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እውነቴ አለነ፣ የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጄኔራል እና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ቦርድ ሰብሳቢ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ፣ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሃይማኖት ዘለቀ፣ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር)፣ የመገናኛ ብዙኃን የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።
ተቀናጀ የሚዲያ ሬጉላቶሪ እና አስተዳደር ስርዓት ቴክኖሎጂ ወደ ተግባር እንዲገባ መደረጉ የባለስልጣኑን እና የዘርፉን ሥራዎች ዘመናዊ ወደ ሆነ አዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግር መሆኑ ተገልጿል።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሃይማኖት ዘለቀ በወቅቱ እንደገለጹት፤ ቴክኖሎጂው የተቋሙን ተልዕኮ ለማሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ አለው።
የተቀናጀ የሚዲያ ሬጉላቶሪ እና የአስተዳደር ስርዓት የመገናኛ ብዙኃን የክትትልና የቁጥጥር ሥርዓትን እንደሚያዘምን ገልጸው፥ ኢትዮጵያ እየተገበረች ካለው የዲጂታላይዜሽን ሥርዓት ጋር የተጣጣመ ነው ብለዋል።
የሐሰተኛ መረጃ ስርጭትንና የጥላቻ ንግግርን መከላከልን በሰው ሰራሽ አስተውሎት በመታገዝ ውጤታማ እንደሚያደርግም ጠቁመዋል።
የሚዲያዎችን ሕጋዊነት ለማረጋገጥ እና በዘርፉ ላይ ግልፅ የሆነ የክትትልና ቁጥጥር ስርዓት በመዘርጋት ረገድ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወትም ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር)፥ ኢንስቲትዩቱ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ ሰው ሠራሽ አስተውሎት ለሁሉም በሚል መሪ ሀሳብ እየሠራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።
የመገናኛ ብዙኃን አሠራርን በማዘመን ሀገራዊ ሚናውን በመወጣት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ዛሬ ይፋ የሆነው የሚዲያ ሬጉላቶሪና አስተዳደር ቴክኖሎጂ ለዘርፉ ዕድገት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን አመልክተዋል።
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 11/2018 (ኢዜአ)፡- ቱሪዝም የኢኮኖሚያችን አንዱ ምሰሶ እንደመሆኑ የሀገራዊ ዕድገታችንን የወደፊት አቅጣጫ እየቀረጸ ያለ ዘርፍ መሆኑ...
Apr 20, 2026
ጅማ፤ ሚያዝያ 6/2018(ኢዜአ)፡- በጅማ የኮደርስ ስልጠና የወሰዱ የመንግሥት ሠራተኞች ቀልጣፋና ዘመናዊ የሕዝብ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ እያገዛቸው መሆኑን...
Apr 14, 2026
አምቦ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን የፍራፍሬ ልማትን የማስፋፋት ስራ በትኩረት እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር ገለጸ።...
Mar 27, 2026
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ጥያቄ ያቀረበችው እ.አ.አ 2003 ነበር። ኢትዮጵያ በወቅቱ ጥያቄውን ካቀረበች በ...
Mar 27, 2026