የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

በጅማ ከተማ ህገወጥ የነዳጅ ግብይትን የመቆጣጠር ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል

Apr 9, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ጅማ ፤መጋቢት 30/2018 (ኢዜአ)፦በጅማ ከተማ ህገወጥ የነዳጅ ግብይትን የመቆጣጠር ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለጸ።

በከተማዋ ነዳጅ በህገወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩ የነበሩ አካላት በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የጅማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የኮሙኒኬሽን ክፍል ሀላፊ ኮማንደር ገዛኸኝ አውግቸው ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በከተማው በነዳጅ ግብይት ህገወጥነትን ለመከላከል ጠንካራ ክትትል እየተደረገ ነው።

በዚህም ትናንት ከለሊቱ ዘጠኝ ሰአት ላይ በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 250 ሊትር ነዳጅ በፀጥታ አካላት ክትትል ተይዟል ብለዋል።


በዚሁ ህገወጥ ተግባር የተጠረጠሩ አምስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም መንግስት ያስቀመጠውን የነዳጅ ሽያጭ መመሪያ በመተላለፍ በህገወጥ መንገድ ቤንዚል በመሸጥ ላይ የነበረ አንድ የነዳጅ ማደያ እንዲታሸግ መደረጉን ጠቁመው በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል ።

ማህበረሰቡ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት የሚንቀሳቀሱ ህገወጥ አካላትን ሲመለከት ለፀጥታ አካላት ጥቆማ በመስጠት ትብብሩን እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ቱሪዝም የሀገራዊ ዕድገታችንን የወደፊት አቅጣጫ እየቀረጸ ያለ ዘርፍ መሆኑን እያስመሰከረ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 

‎አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 11/2018 (ኢዜአ)፡- ቱሪዝም የኢኮኖሚያችን አንዱ ምሰሶ እንደመሆኑ የሀገራዊ ዕድገታችንን የወደፊት አቅጣጫ እየቀረጸ ያለ ዘርፍ መሆኑ...

Apr 20, 2026

የኮደርስ ስልጠና ቀልጣፋና ዘመናዊ የሕዝብ አገልግሎት መስጠት አስችሏል

ጅማ፤ ሚያዝያ 6/2018(ኢዜአ)፡- በጅማ የኮደርስ ስልጠና የወሰዱ የመንግሥት ሠራተኞች ቀልጣፋና ዘመናዊ የሕዝብ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ እያገዛቸው መሆኑን...

Apr 14, 2026

በምዕራብ ሸዋ ዞን የፍራፍሬ ልማትን የማስፋፋት ስራ በትኩረት እየተከናወነ ነው

አምቦ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን የፍራፍሬ ልማትን የማስፋፋት ስራ በትኩረት እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር ገለጸ።...

Mar 27, 2026

ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የደረሰው የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሂደት

በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ጥያቄ ያቀረበችው እ.አ.አ 2003 ነበር። ኢትዮጵያ በወቅቱ ጥያቄውን ካቀረበች በ...

Mar 27, 2026