የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

አዲስ አበባ ሁሉንም አሳታፊ እና አርቆ አሳቢ የሆነ የከተማ ልማት ትልማችን መገለጫ ናት - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) 

Apr 1, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2018(ኢዜአ)፦ አዲስ አበባ ሁሉንም አሳታፊ እና አርቆ አሳቢ የሆነ የከተማ ልማት ትልማችን መገለጫ ናት ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አዲስ አበባ ከዋና ከተማ በላይ ናት! በሚል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።

አዲስ አበባ በፈጣን እንቅስቃሴ ላይ ያለች፣ ወደ ኢትዮጵያ ነገ የመግቢያ በር፤ በፍጥነት እየተለወጠች ያለች የሀገር የልብ ትርታ መሆኗንም አክለዋል።


ፈጣን መሰረተ ልማቶችን በማስፋፋት፣ የዘመናዊ ከተማ መፍትሄዎችን በማቅረብ፣ አካታች በሆነ መልኩ መኖሪያ ቤት በመገንባት እና ዘላቂ ዕድገትን በማረጋገጥ እየሰራን ያለነው ዛሬን ብቻ ሳይሆን ለነገው ትውልድ ጭምር ነው ብለዋል በመልዕክታቸው።

በኢትዮጵያ የሚገኙ ከተሞቻችን ሰዎችን ለማብቃት፣ አቅምን ለመጠቀም እና ዘላቂ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ ቅርጽ ይዘዋል ሲሉም ተናግረዋል።

ሀገራችን ዕድገትና ቅርስ ሳይዛነፉ ጎን ለጎን የሚጓዙባት፤ ጥንታዊ ስልጣኔዎች ለዘመናዊ ስኬት መነሻ የሚሆኑባት ናት ብለዋል በመልዕክታቸው።

ባለሀብቶች በሁሉም አቅጣጫ በተለያዩ ዘርፎች ሰፊና ያልተነኩ ዕድሎችን የሚያገኙባት ባለ እልፍ ጸጋ ሀገር ናት ሲሉም አስታውቀዋል።

ከመዲናዋ አዲስ አበባ ጎዳናዎች እስከ ሀገሪቱ ዳርቻዎች ድረስ በጽናት፣ በብርታት፣ ንቁ እና ልዩ የንግድ አማራጮችን ዝግጁ አድርጋ ኢትዮጵያ ትጠብቃችኋለች ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።


የአፍሪካ የዲፕሎማሲ መናኽሪያ እንደመሆኗ አዲስ አበባ እያደገ ያለውን አኅጉር ከዓለም ጋር ታገናኛለች ሲሉም ገልጸዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)።

ኢትዮጵያ ወደ አፍሪካ ገበያ መግቢያ ስትራቴጂካዊ በር በመሆኗ ለዓለም አቀፍ አጋርነት ማዕከል እንድትሆንም አድርጓታል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ ከዕድሎች በላይ የሆነ ነገርን ይዛለች፤ እሱም አዲስ ነገርን ማግኘትና መግለጥ ነው ብለዋል።

እዚህ ወደፊትን እየገነባን ነው! ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩበኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ፤ ኢትዮጵያን ይጎብኙ፤ ከኢትዮጵያ ጋር አብረው ይደጉ ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ቱሪዝም የሀገራዊ ዕድገታችንን የወደፊት አቅጣጫ እየቀረጸ ያለ ዘርፍ መሆኑን እያስመሰከረ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 

‎አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 11/2018 (ኢዜአ)፡- ቱሪዝም የኢኮኖሚያችን አንዱ ምሰሶ እንደመሆኑ የሀገራዊ ዕድገታችንን የወደፊት አቅጣጫ እየቀረጸ ያለ ዘርፍ መሆኑ...

Apr 20, 2026

የኮደርስ ስልጠና ቀልጣፋና ዘመናዊ የሕዝብ አገልግሎት መስጠት አስችሏል

ጅማ፤ ሚያዝያ 6/2018(ኢዜአ)፡- በጅማ የኮደርስ ስልጠና የወሰዱ የመንግሥት ሠራተኞች ቀልጣፋና ዘመናዊ የሕዝብ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ እያገዛቸው መሆኑን...

Apr 14, 2026

በምዕራብ ሸዋ ዞን የፍራፍሬ ልማትን የማስፋፋት ስራ በትኩረት እየተከናወነ ነው

አምቦ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን የፍራፍሬ ልማትን የማስፋፋት ስራ በትኩረት እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር ገለጸ።...

Mar 27, 2026

ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የደረሰው የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሂደት

በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ጥያቄ ያቀረበችው እ.አ.አ 2003 ነበር። ኢትዮጵያ በወቅቱ ጥያቄውን ካቀረበች በ...

Mar 27, 2026