የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

የኮደርስ ስልጠና የቴክኖሎጂ ዕውቀትና ክህሎት የታጠቀ ተወዳዳሪና ውጤታማ ትውልድ እየፈጠረ ነው

Mar 31, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ድሬደዋ፣ መጋቢት 22/2018(ኢዜአ) ፡-የኮደርስ የስልጠና የቴክኖሎጂ ክህሎትና ዕውቀትን የታጠቀ ተወዳዳሪና ውጤታማ ትውልድ እየፈጠረ መሆኑን የድሬደዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ ተናገሩ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢኒሼቴቭ የሆነው የ5 ሚሊዮን የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና በመላው አገሪቱ የሚገኙ ወጣቶች በተለያዩ የቴክኖሎጂ መስኮች ዕውቀትና ክህሎት ጨብጠው ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ እያስቻለ ይገኛል።

የዚህ ኢንሼቲቭ ተጠቃሚ የሆነው የድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ 36 ሺህ ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ ባከናወናቸው ተግባራት አበረታች ውጤት እየተገኘ ነው።

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የኮደርስ ስልጠና ተወዳዳሪና ውጤታማ ትውልድ ለመፍጠር እያስቻለ ነው።

ለስልጠናው ከተመዘገቡት 36 ሺህ ወጣቶች መካከል 70 በመቶዎቹ ስልጠናውን በብቃትና በንቃት መከታተላቸውን ጠቅሰው ከነዚህ መካከል 59 በመቶዎቹ የምስክር ወረቀት ማግኘታቸውን ተናግረዋል።

እስከ በጀት ዓመቱ ማጠናቀቂያ ድረስ በዘርፉ ስልጠናውን ለመስጠት የተቀመጠውን እቅድ ሙሉ በሙሉ ለማሳካት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

እንደ ምክትል ከንቲባው ገለፃ ኢትዮ ኮደርስ ወጣቶች በቀሰሙት ዕውቀትና ክህሎት ታግዘው ስራ በመፍጠር፣ ሃብት በማፍራት ፣ ብቃታቸውንና ውጤታማነታቸውን እያረጋገጡ ይገኛሉ።

ስልጠናውን ያጠናቀቁ ወጣቶችም በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እና በሲቪል ሰርቪስ ተቋማት ውስጥ የሚሰጡ አገልግሎቶችን በማቀላጠፍ ብቃታቸውን በተግባር እያረጋገጡ መሆናቸውን አንስተዋል።

የተከናወኑት ተግባራት ድሬዳዋን በአገር አቀፍ ደረጃ የተሻለ ውጤት እንድታስመዘግብ ማድረጉን አውስተው በቀሪዎቹ የበጀት ወራት የተሻለ ውጤታማ ስራ ለመስራት ርብርብ እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል።

ስልጠናው የተጣለባቸውን ህዝባዊና መንግስታዊ ተልዕኮዎችን በብቃትና በጥራት ለማከናወን እንዳስቻላቸው ሰልጣኞቹ ገልፀዋል።


በድሬ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሰራተኛ ወጣት ሳራ ሁሴን እንዳለችው፤ የቀሰመችው ዕውቀትና ክህሎት በላቀ ብቃትና ፍጥነት ኃላፊነቷን ለመወጣት አስችሏታል።

የኢትዮ ከደርስ ስልጠና አገልግሎት አሰጣጥን ይበልጥ ፈጣንና ቀልጣፋ ለማድረግ እንዳስቻለም ነው የምትናገረው ።


የስልጠናውን የምስክር ወረቀት ያገኘው የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ሰራተኛ ወጣት ፍቅሩ ዘውዴ በበኩሉ ኢትዮ-ኮደርስ የአዲሱን ትውልድ የቴክኖሎጂ ክህሎት በከፍተኛ ደረጃ እያሳደገ መሆኑን ተናግሯል።

ስልጠናው ተልዕኮን በጥራትና በፍጥነት በማጠናቀቅ የተገልጋዩን እርካታ ለመጨመር ማስቻሉን በመጥቀስ።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ቱሪዝም የሀገራዊ ዕድገታችንን የወደፊት አቅጣጫ እየቀረጸ ያለ ዘርፍ መሆኑን እያስመሰከረ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) 

‎አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 11/2018 (ኢዜአ)፡- ቱሪዝም የኢኮኖሚያችን አንዱ ምሰሶ እንደመሆኑ የሀገራዊ ዕድገታችንን የወደፊት አቅጣጫ እየቀረጸ ያለ ዘርፍ መሆኑ...

Apr 20, 2026

የኮደርስ ስልጠና ቀልጣፋና ዘመናዊ የሕዝብ አገልግሎት መስጠት አስችሏል

ጅማ፤ ሚያዝያ 6/2018(ኢዜአ)፡- በጅማ የኮደርስ ስልጠና የወሰዱ የመንግሥት ሠራተኞች ቀልጣፋና ዘመናዊ የሕዝብ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ እያገዛቸው መሆኑን...

Apr 14, 2026

በምዕራብ ሸዋ ዞን የፍራፍሬ ልማትን የማስፋፋት ስራ በትኩረት እየተከናወነ ነው

አምቦ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን የፍራፍሬ ልማትን የማስፋፋት ስራ በትኩረት እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር ገለጸ።...

Mar 27, 2026

ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የደረሰው የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሂደት

በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ጥያቄ ያቀረበችው እ.አ.አ 2003 ነበር። ኢትዮጵያ በወቅቱ ጥያቄውን ካቀረበች በ...

Mar 27, 2026