🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 15/2018(ኢዜአ)፦ 10ኛው ዓለም አቀፍ የሆርቲካልቸር የንግድ ትርዒት የኢትዮጵያን እምቅ አቅም ለዓለም ገበያ ይበልጥ ለማስተዋወቅና የንግድ ትስስርን ለማጠናከር ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥር የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፍያ ካሳ(ዶ/ር) ገለጹ።
የኢትዮጵያ አበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ አምራችና ላኪዎች ማህበር ከኤች.ፒ.ፒ. ዓለም አቀፍ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ይህ የንግድ ትርዒት ከዛሬ መጋቢት 15 እስከ 17 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

በመክፈቻው የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ ሶፍያ ካሳ(ዶ/ር)፤ ኢትዮጵያ በአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ ያላትን እምቅ አቅም ይበልጥ ለማሳደግ መንግስት ለግሉ ዘርፍ ምቹ ምህዳር መፍጠሩን ገልጸዋል።
ለዚህም ዘርፉን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚያደርገውን የግብርናና ገጠር ልማት ፖሊሲ እንዲሁም የአበባ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ስትራቴጂ ተቀርጾ ወደ ሥራ መገባቱን ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ ወደ ውጭ ከምትልካቸው የሆርቲካልቸር ምርቶች ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እያገኘች መሆኑን ገልጸው፤ ይህ የንግድ ትርዒት አምራቾችን ከዓለም አቀፍ ገዢዎች ጋር በቀጥታ በማገናኘት እንደ ትልቅ ድልድይ ሆኖ ያገለግላል ብለዋል።
የኢትዮጵያ አበባ አትክልትና ፍራፍሬ አምራቾችና ላኪዎች ማህበር ዋና ዳይሬክተር ነጋ መኳንንት በበኩላቸው፤ ኤክስፖው ምርትና አገልግሎትን ከማስተዋወቅ ባለፈ በዘርፉ ያሉ ተዋናዮችን በአንድ ጣሪያ ስር በማገናኘት የንግድ ትስስርን ለማጠናከር ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህም ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ የተደገፈና ለዓለም ገበያ ተወዳዳሪ የሆነ የኢንዱስትሪ ግንባታ ለማካሄድ ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑንም አብራርተዋል።

የሆርቲካልቸር ዘርፍ ከቡና ቀጥሎ ለኢትዮጵያ ዋነኛው የውጭ ምንዛሪ ምንጭ ሲሆን፤ ባለፈው በጀት ዓመት 564 ነጥብ 89 ሚሊየን ዶላር ለሀገሪቱ ማስገኘቱ ጠቅሰዋል፡፡
ለሦስት ቀናት በሚቆየው በዚህ ንግድ ትርዒት ላይ ከ50 በላይ ሀገራት የተወከሉ ሲሆን፤ ከ150 በላይ የሀገር ውስጥና የውጭ አልሚ ባለሀብቶች፣ አምራቾች፣ የቴክኖሎጂ አቅራቢዎችና የፋይናንስ ተቋማት እንደሚሳተፉ ታውቋል።
በቆይታው ሰው ሰራሽ አስተውሎት(AI)፣ ዘላቂ ፋይናንስ፣ የምግብ ደህንነት፣ የባህር ጭነት ሎጂስቲክስ እና የአየር ንብረት ለውጥን በሚቋቋሙ የቴክኖሎጂ ፈጠራዎች ላይ ያተኮሩ ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸው ውይይቶች እንደሚካሄዱ ይጠበቃል።
አምቦ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን የፍራፍሬ ልማትን የማስፋፋት ስራ በትኩረት እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር ገለጸ።...
Mar 27, 2026
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ጥያቄ ያቀረበችው እ.አ.አ 2003 ነበር። ኢትዮጵያ በወቅቱ ጥያቄውን ካቀረበች በ...
Mar 27, 2026
Jul 17, 2025
Apr 24, 2025