🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ የካቲት 8/2018 (ኢዜአ)፡- ለአፍሪካ ብልጽግና እና መረጋጋት በውኃ ዘርፍ ላይ በቁርጠኝነት ኢንቨስት ማድረግ እንደሚገባ በአፍሪካ ኅብረት የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ብሉ ኢኮኖሚ እና የዘላቂ አካባቢ ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ አስገነዘቡ።
39ኛው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ “ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሐሳብ በኅብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
ኮሚሽነር ሞሰስ ቪላካቲ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ውኃ እና የንጽህና አጠባበቅ ለአፍሪካ ልማት እና ለኢኮኖሚ ሽግግር መሠረታዊ ጉዳዮች ናቸው።
አፍሪካ በዘርፉ በየዓመቱ በቢሊየን የሚቆጠር ዶላር የገንዘብ እጥረት እንዳለባት ጠቁመው፤ ይህም የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት እና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም እንቅፋት መሆኑን አንስተዋል።
ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት የአፍሪካ ኅብረት 39ኛው የመሪዎች ጉባዔ መሪ ሐሳብ "ዘላቂ የውኃ አቅርቦት እና አስተማማኝ የንጽህና ሥርዓቶችን በማረጋገጥ አጀንዳ 2063ን ማሳካት" ተብሎ የተመረጠውም ለዚህ ነው ብለዋል።
በጉባዔው ለኢንቨስትመንት ዝግጁ የሆኑ ፕሮጀክቶች መቅረባቸውን ጠቅሰው፤ እነዚህም በዓመት በርካታ ቢሊየን ዶላር የሚደርስ የኢንቨስትመንት ቃል ኪዳን ተገኝቶላቸዋል ሲሉ ገልጸዋል።
ሀገራት የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋሙ የውኃ ፕሮግራሞችን እንዲያዘጋጁ የሚያግዙ መመሪያዎች እና የኢንቨስትመንት ሂደቱን ለመከታተል የሚያስችል የውጤት መመዝገቢያ ይፋ መደረጉንም ጠቅሰዋል።
ለአፍሪካ ብልጽግና እና መረጋጋት በቁርጠኝነት በውኃ ዘርፍ ላይ በቆራጥነት ኢንቨስት ማድረግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
አምቦ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን የፍራፍሬ ልማትን የማስፋፋት ስራ በትኩረት እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር ገለጸ።...
Mar 27, 2026
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ጥያቄ ያቀረበችው እ.አ.አ 2003 ነበር። ኢትዮጵያ በወቅቱ ጥያቄውን ካቀረበች በ...
Mar 27, 2026
Jul 17, 2025
Apr 24, 2025