🔇Unmute
ጨፋ ሮቢት፤ ህዳር 23/2018(ኢዜአ )፡- በጨፋ ሮቢት ከተማ ከ33 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የተለያዩ መሰረተ ልማቶች ግንባታ እየተካሄደ መሆኑን የከተማው ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ሰይድ መሀመድ ገለፁ።
የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ፣ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ፣ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ሌሎችም ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በአማራ ክልል በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።

የከተማው ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ሰይድ መሀመድ በወቅቱ እንደገለፁት በከተማው ህብረተሰቡን በማስተባበር የተለያዩ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ ነው።
በዘንድሮው በጀት ዓመት ከ33 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የጌጠኛ ድንጋይ ንጣፍ ጨምሮ የመንገድ፣ የፍሳሽ መውረጃና የሌሎች የመሰረተ ልማቶች ግንባታ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል ።
በተጨማሪም የአቅመ ደካማ ህብረተሰብ ክፍሎች መኖሪያ ቤቶች ግንባታ እየተካሄደ መሆኑን አመልክተዋል ።
የመሰረት ልማቶች በተያዘላቸው ጊዜ በጥራት ተገንብተው እንዲጠናቀቁ ክትትልና ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል።

ሚኒስትሮቹን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎቹ የጨፋ ሮቢት የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን የስራ እንቅስቃሴም ተመልክተዋል።
አምቦ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን የፍራፍሬ ልማትን የማስፋፋት ስራ በትኩረት እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር ገለጸ።...
Mar 27, 2026
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ጥያቄ ያቀረበችው እ.አ.አ 2003 ነበር። ኢትዮጵያ በወቅቱ ጥያቄውን ካቀረበች በ...
Mar 27, 2026
Jul 17, 2025
Apr 24, 2025