🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 18/2018(ኢዜአ)፦ በፌደራል መንግስት ብቻ 26ሺህ 500 ኪሎ ሜትር መንገድ እየተገነባ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ገለጹ።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፕሮጀክቶች ክትትልን በሚመለከት በሰጡት ማብራሪያ ኢትዮጵያ ውስጥ 346 የመንገድ ፕሮጀክቶች በግንባታ ላይ መሆናቸውን ጠቁመው 26ሺህ 500 ኪሎ ሜትር መንገድ በፌደራል መንግስት ብቻ እየተገነባ ይገኛል ብለዋል።
እነዚህን ሁሉ ፕሮጀክቶች በተመሳሳይ መከታተል እጅግ አስቸጋሪ ስራ መሆኑን ጠቅሰው ግድብን በሚመለከትም ከ200 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው 14 መካከለኛና አነስተኛ የግድብ ፕሮጀክቶች እንዳሉም ገልጸዋል።
መንግስት የማስፈጸም አቅሙን በማሳደግ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ እየሰራ ነው ሲሉም ተናግረዋል።
ከተረጂነት መላቀቅን በተመለከተ ሲገልጹም ተረጂነት የመስራት ጉልበትን የሚበላ ካንሰር ነው ብለዋል።
በስንዴ፣ ፍራፍሬና ሌማት ትሩፋት የምንሰራው ስራም ከተረጂነት ለመላቀቅ ባለን ቁርጠኝነት ነው ያሉ ሲሆን ስለዚህ ጨከን ብለን ተረጂነት ይበቃናል ማለት አለብን ነው ያሉት።
ደግሞም እንችላለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እርዳታ ብዙ ጣጣ በውስጡ አለበት ኢትዮጵያን መለመኛ ማድረግ መቆም አለበት ነው ያሉት በማብራሪያቸው።
የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ እድገት በሚመለከትም በኢትዮጵያ የመጣው የእሳቤ ለውጥ በርካታ እምርታዎችን አምጥቷል ብለዋል።
ኢትዮጵያ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2032 በአፍሪካ 2ኛ፣ በ2036 ደግሞ ከአፍሪካ የመጀመሪያውን ኢኮኖሚ እንደምትገነባ ጥርጥር የለኝም ሲሉ ገልጸዋል።
አምቦ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን የፍራፍሬ ልማትን የማስፋፋት ስራ በትኩረት እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ አስተዳደር ገለጸ።...
Mar 27, 2026
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ጥያቄ ያቀረበችው እ.አ.አ 2003 ነበር። ኢትዮጵያ በወቅቱ ጥያቄውን ካቀረበች በ...
Mar 27, 2026
Jul 17, 2025
Apr 24, 2025